ጌታ ፡ በማዳንህ ፡ ደስ ፡ ብሎናል (Gieta Bemadaneh Des Belonal)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

1. ማኅተሙን ፡ ከፈተ ፡ ጌታ ፡ የታሰረውን
የታሰረውን ፡ ምርኮኛ ፡ ፈታ
ቀንበሩን ፡ ሰበረ ፡ ጌታ ፡ ሰባበረው
የጠላትን ፡ ኃይል ፡ አረጋገጠና
የማዳኑን ፡ ኃይል ፡ ለልጆቹ ፡ አሳየ ፡ እንደገና

አዝ፦ ጌታ ፡ በማዳንህ ፡ ደስ ፡ ብሎናል
አሜን ፡ ደስ ፡ ብሎናል (፪x)
ጌታ ፡ በማዳንህ ፡ ደስ ፡ ብሎናል
ክብር ፡ ሃሌሉያ ፡ ክብር
ማዳን ፡ እና ፡ ኃያል ፡ ለበጉ ፡ ነው
አሜን ፡ ለኢየሱስ ፡ ነው

2. ሕዝብን ፡ ለዓለም ፡ ከዘር ፡ ከነገድ ፡ ከቋንቋ ፡ ሁሉ
ከቋንቋ ፡ ሁሉ ፡ በአንድ ፡ ላይ ፡ ሲያደርግ
የዘርን ፡ ልዩነት ፡ ሰብሮ ፡ ጠላት ፡ ሲወድቅ
ጨዋና ፡ ባሪያ ፡ ነጭ ፡ ጥቁር ፡ ሁሉ
በአንድ ፡ ላይ ፡ ሆነው ፡ ለኢየሱስ ፡ ክብር ፡ ምሥጋና ፡ ሰዉ

አዝ፦ ጌታ ፡ በማዳንህ ፡ ደስ ፡ ብሎናል
አሜን ፡ ደስ ፡ ብሎናል (፪x)
ጌታ ፡ በማዳንህ ፡ ደስ ፡ ብሎናል
ክብር ፡ ሃሌሉያ ፡ ክብር
ማዳን ፡ እና ፡ ኃያል ፡ ለበጉ ፡ ነው
አሜን ፡ ለኢየሱስ ፡ ነው

3. የከበረ ፡ ታላቅ ፡ ድንቅ ፡ ጌታ ፡ ለዘለዓለም
ለዘለዓለም ፡ ሞትን ፡ ድል ፡ ረታ
አጋንንት ፡ ሲንጫጫ ፡ ሲጮህ ፡ ሲንገላታ
ከኃያላን ፡ ጋር ፡ ምርኮን ፡ ተካፍሎ
ኢየሱስ ፡ ብቅ ፡ አለ ፡ በድል ፡ መለከት ፡ ወንጌል ፡ ሰብኮ

አዝ፦ ጌታ ፡ በማዳንህ ፡ ደስ ፡ ብሎናል
አሜን ፡ ደስ ፡ ብሎናል (፪x)
ጌታ ፡ በማዳንህ ፡ ደስ ፡ ብሎናል
ክብር ፡ ሃሌሉያ ፡ ክብር
ማዳን ፡ እና ፡ ኃያል ፡ ለበጉ ፡ ነው
አሜን ፡ ለኢየሱስ ፡ ነው

4. ዛሬም ፡ ጌታ ፡ በዕለት ፡ ኑሯችን ፡ ፈጥኖ ፡ እየመጣ
ፈጥኖ ፡ እየመጣ ፡ ይደግፈናል
ሐዘናችንን ፡ ሁሉ ፡ ጌታ ፡ ይካፈላል
ወንጌል ፡ ስንዘራ ፡ በላብና ፡ በእንባ
ፍሬ ፡ ያሳየናል ፡ በድካማችን ፡ እርሱ ፡ እየገባ

አዝ፦ ጌታ ፡ በማዳንህ ፡ ደስ ፡ ብሎናል
አሜን ፡ ደስ ፡ ብሎናል (፪x)
ጌታ ፡ በማዳንህ ፡ ደስ ፡ ብሎናል
ክብር ፡ ሃሌሉያ ፡ ክብር
ማዳን ፡ እና ፡ ኃያል ፡ ለበጉ ፡ ነው
አሜን ፡ ለኢየሱስ ፡ ነው