ጌታ ፡ በአንተ ፡ ደስ ፡ ይለናል (Gieta Bante Des Yilenal)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፦ ጌታ ፡ በአንተ ፡ ደስ ፡ ይለናል
ሁልጊዜ ፡ ደስ ፡ ይለናል
ኢየሱስ ፡ በአንተ ፡ ደስ ፡ ይለናል
ሁልጊዜ ፡ ደስ ፡ ይለናል

1. በዓለም ፡ መከራ ፡ ውስጥ ፡ ብናልፍ
በሐዘን ፡ በትር ፡ ብንገረፍ
ብናጣ ፡ ወይም ፡ ደግሞ ፡ ብናተርፍ
ምንም ፡ ቢሆን ፡ ምንም ፡ ደስተኞች ፡ ነን
በሚሆነው ፡ ሁሉ ፡ ሰላም ፡ አለን
ከሁሉ ፡ የሚበልጥ ፡ ስላገኘን
በመስቀሉ ፡ ፍቅር ፡ እንረካለን

አዝ፦ ጌታ ፡ በአንተ ፡ ደስ ፡ ይለናል
ሁልጊዜ ፡ ደስ ፡ ይለናል
ኢየሱስ ፡ በአንተ ፡ ደስ ፡ ይለናል
ሁልጊዜ ፡ ደስ ፡ ይለናል

2. በእርሱ ፡ ደስ ፡ የሚለኝ ፡ የምወደው
ልቤ ፡ ያረፈበት ፡ ልጄ ፡ ይህ ፡ ነው
የሚለው ፡ ድምጽ ፡ ከሰማይ ፡ የመጣው
እግዚአብሔር ፡ እንኳን ፡ ሁሉ ፡ እያለው
ነገር ፡ ግን ፡ ደስታው ፡ በልጁ ፡ ነው
የልጆቹም ፡ ሰላምና ፡ ደስታ
በሌላ ፡ አይደለም ፡ ነው ፡ በጌታ

አዝ፦ ጌታ ፡ በአንተ ፡ ደስ ፡ ይለናል
ሁልጊዜ ፡ ደስ ፡ ይለናል
ኢየሱስ ፡ በአንተ ፡ ደስ ፡ ይለናል
ሁልጊዜ ፡ ደስ ፡ ይለናል

3. በዚህ ፡ ዓለም ፡ ያሉት ፡ ሞኞች ፡ ናቸው
በሚጠፋ ፡ ነገር ፡ ነው ፡ ደስታቸው
በሚያልፍ ፡ ነገር ፡ ነው ፡ እርካታቸው
እኛ ፡ ግን ፡ በጌታ ፡ ደስ ፡ ይለናል
ከእርሱ ፡ ባገኘነው ፡ እረክተናል
ፊታችን ፡ አይዞርም ፡ ወደ ፡ ዓለም
ዘላቂ ፡ ደስታ ፡ በዚያ ፡ የለም

አዝ፦ ጌታ ፡ በአንተ ፡ ደስ ፡ ይለናል
ሁልጊዜ ፡ ደስ ፡ ይለናል
ኢየሱስ ፡ በአንተ ፡ ደስ ፡ ይለናል
ሁልጊዜ ፡ ደስ ፡ ይለናል

4. በረሃብ ፡ በጥማት ፡ ደስ ፡ ይለናል
በማግኘት ፡ በማጣት ፡ ደስ ፡ ይለናል
በመከራም ፡ ሰዓት ፡ ደስ ፡ ይለናል
ተስፋ፡ ቢጨላልም ፡ ደስ ፡ ይለናል
ሸለቆው ፡ ባይሞላም ፡ ደስ ፡ ይለናል
ዕቅድ ፡ ባይሳካም ፡ ደስ ፡ ይለናል
ሁልጊዜ ፡ በጌታ ፡ ደስ ፡ ይለናል

አዝ፦ ጌታ ፡ በአንተ ፡ ደስ ፡ ይለናል
ሁልጊዜ ፡ ደስ ፡ ይለናል
ኢየሱስ ፡ በአንተ ፡ ደስ ፡ ይለናል
ሁልጊዜ ፡ ደስ ፡ ይለናል