From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
|
|
ሌሎች ፡ የድሮ ፡ መዝሙሮች (Other Classic Mezmur Lyrics)
|
|
1. ጌታ ፡ አምላኬ ፡ እንዴት ፡ እገረማለሁ
ሳስብ ፡ ሳለሁ ፡ የእጆችህን ፡ ፍጥነት
ከዋክብትን ፡ ሳይ ፡ ነጐድጓድን ፡ ስሰማ
የአንተ ፡ ስልጣን ፡ በህዋህ ፡ ውስጥ ፡ ታየኝ
አዝ፦ ነፍሴ ፡ ለአንተ ፡ መዝሙር ፡ ታቀርባለች (፪x)
ኃያል ፡ ግሩም ፡ ታላቅ ፡ አምላክ
2. ጥቅጥቅ ፡ ባለው ፡ ደን ፡ ውስጥ ፡ ስመላለስ
የወፎችን ፡ ዝማሬ ፡ ስሰማ
ሳይ ፡ ወደ ፡ ታች ፡ ከፍ ፡ ካለው ፡ ተራራ ፡ ላይ
ምንጩ ፡ ሲፈልቅ ፡ ነፋሱም ፡ ሽው ፡ ሲል
አዝ፦ ነፍሴ ፡ ለአንተ ፡ መዝሙር ፡ ታቀርባለች (፪x)
ኃያል ፡ ግሩም ፡ ታላቅ ፡ አምላክ
3. ሳስብ ፡ ሳለሁ ፡ አብ ፡ ለልጁ ፡ ሳይሳሳ
እንደላከው ፡ ሊሞት ፡ በእኔ ፡ ፈንታ
በመስቀል ፡ ላይ ፡ ሸክሜን ፡ በደስታ ፡ ችሎ
ተሰቃየ ፡ ኃጢአቴን ፡ ለመውሰድ
አዝ፦ ነፍሴ ፡ ለአንተ ፡ መዝሙር ፡ ታቀርባለች (፪x)
ኃያል ፡ ግሩም ፡ ታላቅ ፡ አምላክ
4. ክርስቶስ ፡ ኢየሱስ ፡ በታላቅ ፡ ክብር ፡ መጥቶ
ይዞኝ ፡ ሲሄድ ፡ ደስታዬ ፡ እንዴት ፡ ይሆን
ከዚያም ፡ ለእርሱ ፡ በምሥጋና ፡ እሰግዳለሁ
ለታላቁ ፡ ግሩም ፡ ኃያል ፡ አምላክ
አዝ፦ ነፍሴ ፡ ለአንተ ፡ መዝሙር ፡ ታቀርባለች (፪x)
ኃያል ፡ ግሩም ፡ ታላቅ ፡ አምላክ
|