ጌታ ፡ አምላካችን ፡ አንተው ፡ ሥራበት (Gieta Amlakachin Antew Sirabet)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

አዝ ፣
ጌታ ፡ አምላካችን ፡ አንተው ፡ ሥራበት
በታላቅ ፡ ክንድህ ፡ ተመላለስበት
ጐስቋላነታችንን ፡ በደምህ ፡ ሸፍነህ
በዚህ ፡ ሥፍራ ፡ ክበር ፡ ስለ ፡ ስምህ

ከፍ ፡ በል ፡ ጌታችን ፡ ክብርህ ፡ ያስተጋባ
ቀድሰን ፡ በደምህ ፡ ምራ ፡ ይህን ፡ ስብሰባ
ታላቅነትህን ፡ እንየው ፡ እባክህ
አብራ ፡ መብራትህን ፡ ያንጸባርቅ ፡ ሞገስህ

አዝ ፣
ጌታ ፡ አምላካችን ፡ አንተው ፡ ሥራበት
በታላቅ ፡ ክንድህ ፡ ተመላለስበት
ጐስቋላነታችንን ፡ በደምህ ፡ ሸፍነህ
በዚህ ፡ ሥፍራ ፡ ክበር ፡ ስለ ፡ ስምህ

ሥራ ፡ አምላካችን ፡ ክንድህም ፡ ይዘርጋ
በበደላችን ፡ ጦስ ፡ በርህን ፡ አትዝጋ
በያንዳንዳችን ፡ ልብ ፡ ኢየሱስ ፡ ተመላለስ
ስብሰባችንን ፡ ባርክ ፡ ፊትህንም ፡ መልስ

አዝ ፣
ጌታ ፡ አምላካችን ፡ አንተው ፡ ሥራበት
በታላቅ ፡ ክንድህ ፡ ተመላለስበት
ጐስቋላነታችንን ፡ በደምህ ፡ ሸፍነህ
በዚህ ፡ ሥፍራ ፡ ክበር ፡ ስለ ፡ ስምህ

ባርያህን ፡ ባርከው ፡ ቃልህን ፡ ይናገር
በውስጡ ፡ ግስጸን ፡ ምሥክርህንም ፡ ይንገር
በሕዝብህ ፡ ፊት ፡ ቆሞ ፡ ደግሞ ፡ ለሚመራው
ፀጋህን ፡ አብዛለት ፡ በረከትህን ፡ ሙላው

አዝ ፣
ጌታ ፡ አምላካችን ፡ አንተው ፡ ሥራበት
በታላቅ ፡ ክንድህ ፡ ተመላለስበት
ጐስቋላነታችንን ፡ በደምህ ፡ ሸፍነህ
በዚህ ፡ ሥፍራ ፡ ክበር ፡ ስለ ፡ ስምህ

መዘምራንን ፡ ባርክ ፡ በደምህ ፡ ከልለህ
ለሕዝብህ ፡ በረከት ፡ ይዋሉ ፡ ለክብርህ
የሚዘምሩትን ፡ ለክብርህ ፡ አውለው
ለክርስቲያን ፡ ሁሉ ፡ ክንድህ ፡ እንዲታየው

አዝ ፣
ጌታ ፡ አምላካችን ፡ አንተው ፡ ሥራበት
በታላቅ ፡ ክንድህ ፡ ተመላለስበት
ጐስቋላነታችንን ፡ በደምህ ፡ ሸፍነህ
በዚህ ፡ ሥፍራ ፡ ክበር ፡ ስለ ፡ ስምህ