ገስግሶ ፡ ሲያልፍ ፡ ቀናችን (Gesgiso Siyalf Qenachin)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ገስግሶ ፡ ሲያልፍ ፡ ቀናችን
በአምላክ ፡ ቃል ፡ ሠርክ ፡ እንጽና
እርሱ ፡ ነው ፡ የሚበራልን
በዚህ ፡ ዓለም ፡ ጨለማ
ከጥንት ፡ ዘመን ፡ ጀምሮ
ኃይልን ፡ ደስታን ፡ ሰጥቶ
በሰማይ ፡ በሚያገባ
በዚህ ፡ ቃል ፡ ሠርክ ፡ እንመራ

በዚህ ፡ ዓለም ፡ ስንዋትት
እንደ ፡ ጥንቱ ፡ ቅዱሣን
ቅዱስ ፡ ቃሉን ፡ ለማዳመጥ
እንሰብሰብ ፡ ሲጠራን
አባት ፡ ከልጆች ፡ ጋራ
ያቅርብለት ፡ ምሥጋና
በየውሃቱ ፡ እንዲያየን
ዘወትር ፡ ተግተን ፡ እንለምን

ባርከነ ፡ ጠብቀነ
ፀጋን ፡ ሞገስን ፡ ስጠነ
ዞትር ፡ በምክርህ ፡ ምራነ
በመንገድ ፡ ብርሃን ፡ ሁነን
መልስልን ፡ ፊትህን
ሰልምህን ፡ አካፍለን
ሥሉስ ፡ አምላክ ፡ ስለ ፡ ፍቅሩ
ይመስገን ፡ በዓለም ፡ ሁሉ