ግሩም ፡ ድንቅ ፡ አምላክ ፡ ነው (Gerum Denq Amlak New)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

1. በማዕበል ፡ በሞገድ ፡ መንገድ ፡ አለው
በባሕር ፡ በእሳት ፡ መንገድ ፡ አለው
በሞት ፡ ጥላ ፡ መሃል ፡ ኃይል ፡ የእርሱ ፡ ነው
እግዚአብሔር ፡ በስራው ፡ ድንቅ ፡ ነው

አዝ፦ ግሩም ፡ ድንቅ ፡ አምላክ ፡ ነው ፡ የማመልከው
ሠማይና ፡ ምድር ፡ የሚገዛው
ዘመናት ፡ ሲያልፉ ፡ እርሱ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው
በዘለዓለም ፡ ክብር ፡ የሚኖረው

2. የምድር ፡ ሊቃውንትም ፡ ጠቢባን
የጦር ፡ አበጋዞች ፡ ኃያላን
ነገሥታት ፡ ቢሆኑ ፡ የዓለም ፡ ኃይላት
አልቻሉም ፡ አምላኬን ፡ ሊቋቋሙት

አዝ፦ ግሩም ፡ ድንቅ ፡ አምላክ ፡ ነው ፡ የማመልከው
ሠማይና ፡ ምድር ፡ የሚገዛው
ዘመናት ፡ ሲያልፉ ፡ እርሱ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው
በዘለዓለም ፡ ክብር ፡ የሚኖረው

3. ዓለም ፡ ሳይፈጠር ፡ የነበረ
በዘመናት ፡ ሁሉ ፡ የከበረ
ሁሉን ፡ አሳልፎ ፡ የሚኖረው
ፍጻሜው ፡ አያልቅም ፡ ዘለዓለም ፡ ነው

አዝ፦ ግሩም ፡ ድንቅ ፡ አምላክ ፡ ነው ፡ የማመልከው
ሠማይና ፡ ምድር ፡ የሚገዛው
ዘመናት ፡ ሲያልፉ ፡ እርሱ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው
በዘለዓለም ፡ ክብር ፡ የሚኖረው

4. የብስንና ፡ ባሕርን ፡ የፈጠረ
ከዋክብትን ፡ በጠፍር ፡ ያኖረ
የአማልክት ፡ አምላክ ፡ አምላኬ ፡ ነው
ምድርና ፡ ሞላዋ ፡ የእርሱ ፡ ናቸው

አዝ፦ ግሩም ፡ ድንቅ ፡ አምላክ ፡ ነው ፡ የማመልከው
ሠማይና ፡ ምድር ፡ የሚገዛው
ዘመናት ፡ ሲያልፉ ፡ እርሱ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው
በዘለዓለም ፡ ክብር ፡ የሚኖረው