From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
|
ሌሎች ፡ የድሮ ፡ መዝሙሮች (Other Classic Mezmur Lyrics)
|
|
አዝ፦ ጋሻ ፡ ጦርህን ፡ አንሣ ፡ እግዚአብሔር
የዲያብሎስን ፡ ምሽግ ፡ አፈራርስ ፡ ምሽጉን ፡ አፈራርስ
ቀስቱን ፡ ስበርልን ፡ ፍላፃውን ፡ መልስ
በታላቅ ፡ ስምህን ፡ የዲያብሎስን ፡ ሰፈር ፡ ይተራመስ
1. ጦርን ፡ አስከስቶ ፡ የከበበንን
በቀኝ ፡ በግራ ፡ የወረሩንን
የሚያውከንን ፡ የዲያብሎስ ፡ መንጋ
በታላቅ ፡ ስምህ ፡ በጦርህ ፡ ይወጋ
አዝ፦ ጋሻ ፡ ጦርህን ፡ አንሣ ፡ እግዚአብሔር
የዲያብሎስን ፡ ምሽግ ፡ አፈራርስ ፡ ምሽጉን ፡ አፈራርስ
ቀስቱን ፡ ስበርልን ፡ ፍላፃውን ፡ መልስ
በታላቅ ፡ ስምህን ፡ የዲያብሎስን ፡ ሰፈር ፡ ይተራመስ
2. በነጐድጓድ ፡ ውረድ ፡ በኃይልህ ፡ ተነሣ
የአጋንንትን ፡ ሠፈር ፡ አሳጣው ፡ መድረሻ
በደምህ ፡ የተዋጀውን ፡ ሕዝብህን ፡ የሚያውኩ
በኢየሱስ ፡ ደም ፡ በስሙ ፡ ይድቀቁ
አዝ፦ ጋሻ ፡ ጦርህን ፡ አንሣ ፡ እግዚአብሔር
የዲያብሎስን ፡ ምሽግ ፡ አፈራርስ ፡ ምሽጉን ፡ አፈራርስ
ቀስቱን ፡ ስበርልን ፡ ፍላፃውን ፡ መልስ
በታላቅ ፡ ስምህን ፡ የዲያብሎስን ፡ ሰፈር ፡ ይተራመስ
3. በግርማህ ፡ በክብርህ ፡ በኃይልህ ፡ ውረድ
ምድር ፡ ትገዛልህ ፡ ተራራም ፡ ይናድ
ና ፡ አግዘን ፡ ጌታ ፡ ጠላት ፡ ይደናገጥ
በመስቀሉ ፡ ኃይል : ዲያብሎስ ፡ ይረገጥ
አዝ፦ ጋሻ ፡ ጦርህን ፡ አንሣ ፡ እግዚአብሔር
የዲያብሎስን ፡ ምሽግ ፡ አፈራርስ ፡ ምሽጉን ፡ አፈራርስ
ቀስቱን ፡ ስበርልን ፡ ፍላፃውን ፡ መልስ
በታላቅ ፡ ስምህን ፡ የዲያብሎስን ፡ ሰፈር ፡ ይተራመስ
4. የወንጌል ፡ እውነት ፡ የሚከላልስ
ሕዝቡን ፡ የሚለያይ ፡ የክፉ ፡ መንፈስ
በምድርም ፡ የዘራውም ፡ የጨለማ ፡ ሥራ
በመስቀሉ ፡ ኃይል ፡ ይብነን ፡ እንዳቧራ
|