ፈተናን ፡ አሸንፍ (Fetenan Ashenef)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ፈተናን ፡ አሸንፍ ፡ በአምላክ ፡ ፀጋ
በየጊዜው ፡ ተግተህ ፡ በዕምነት ፡ ተቋቋም
ልብህም ፡ በአንዳች ፡ አያመንታ
ኢየሱስን ፡ ብቻ ፡ እይ
ከቶ ፡ አትወድቅም

አዝ ፡
አዳኙን ፡ አቅርበው ፡
እርሱ ፡ ኃይል ፡ እንዲሰጥህ
በፈተና ፡ አዳኝህ ፡
ከአንተ ፡ ጋር ፡ ይሆናል

ከክፉ ፡ ምኞት ፡ ራቅ
መጥፎ ፡ ቃላት ፡ ሽሽ
የአምላክን ፡ ሥም ፡ አክብር
ትዕቢትን ፡ አርቅ
ትሑትና ፡ ቅን ፡ ሁን
ደግ ፡ ቸርም ፡ ታጋሽ
ኢየሱስን ፡ ብቻ ፡ እይ
ከቶ ፡ አትወድቅም

አዝ ፡
አዳኙን ፡ አቅርበው ፡
እርሱ ፡ ኃይል ፡ እንዲሰጥህ
በፈተና ፡ አዳኝህ ፡
ከአንተ ፡ ጋር ፡ ይሆናል

ድል ፡ ለነሳ ፡ ሁሉ
አክሊል ፡ ይሰጣል
በዕምነት ፡ ብንጠጋው ፡ አያሳፍርም
እርሱ ፡ አዳኛችን ፡ አብሮን ፡ ይሆናል
ለሚገጥመን ፡ ሁሉ ፡ ኃይል ፡ ይሰጠናል

አዝ ፡
አዳኙን ፡ አቅርበው ፡
እርሱ ፡ ኃይል ፡ እንዲሰጥህ
በፈተና ፡ አዳኝህ ፡
ከአንተ ፡ ጋር ፡ ይሆናል