ፈጣሪ ፡ ንጉሤ (Fetari Negusie)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ፈጣሪ ፡ ንጉሤ ፡ ሁሉን ፡ የሰጠኸኝ
በረከት ፡ ይፈልቅልኛል ፡ አንተ ፡ የላክህልኝ (፪x)

እኔ ፡ የጅህ ፡ ፍጥረት ፡ በአንተ ፡ ብቻ ፡ ስኖር
ላደረግህልኙ ፡ ጥቅም ፡ ሳመሰግንህ ፡ ልኑር (፪x)

ሁሉ ፡ የአንተ ፡ ሲሆን ፡ አምላኬ ፡ ምን ፡ ልስጥህ?
ፍቅርህ ፡ ይፈልግብኛል ፡ እንዳመሰግንህ (፪x)

በአምላካዊ ፡ ኃይል ፡ ፀጋህ ፡ ነፍሴን ፡ ያንቃት
ነገሬም ፡ ምኞቴም ፡ ቀኔም ፡ ለአንተ ፡ ይሁን (፪x)