From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
|
ሌሎች ፡ የድሮ ፡ መዝሙሮች (Other Classic Mezmur Lyrics)
|
|
ፈርዖን ፡ የእሥራኤል ፡ ጠላት
በባሕር ፡ እንደቀረ
እንዲሁም ፡ የዓለም ፡ ኃጢአት
___ ኦ ! ተዓምራት ____
በክርስቶስ ፡ ደም ፡ ተሻረ
በባሕር ፡ የተጣለ ፡ ፍም
ቶሎ ፡ እንደሚጠፋ
ጠፋልን ፡ መከራችንም
ተቀበረም
ከእንግዲህ ፡ አይገኝም
ተፈጸመና ፡ ዓለሙ
ከከባድ ፡ ዕዳው ፡ ዳነ
ቢጠጋም ፡ ወደ ፡ መስቀሉ
በዕምነቱ
ዕለቱን ፡ ብጹዕ ፡ ሆነ
ምዕመንም ፡ የምሥራቹን
ይቀበላል ፡ ተደንቆ
ሌላም ፡ ይሰማል ፡ ነግበሩን
ግን ፡ ምሥጢሩን
አያውቅም ፡ ቃሉን ፡ አውቆ
ግን ፡ ከዓለም ፡ አንዱ ፡ እኔ ፡ ነኝ
ስለ ፡ እኔም ፡ ኢየሱስ ፡ ሞተ
በጽድቁም ፡ ስለሸፈነኝ
አጸደቀኝ
ከኃጢአቴ ፡ ሁሉ
የሰይጣን ፡ ፍትወት ፡ በልቤ
እስከማይቻል ፡ ቢሆንም
ሰላም ፡ ላገኝ ፡ ከችግሬ
በመድኅኔ
ከሞት ፡ ፍርሃት ፡ ልዳንም
|