ፍርዳችንን ፡ የወሰድኸው (Ferdachenen Yewesedkew)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ፍርዳችንን ፡ የወሰድኸው
መስቀልን ፡ የተሸከምኸው
ከሞትም ፡ ኃይል ፡ ያወጣኸን
ኦ! ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ አድምጸን
ኦ! የሞትህልን ፡ አድነን
ስማልን ፡ ጸሎታችንን

ታላቅ ፡ ሥራህ ፡ ተፈጸመ
ፍርድ ፡ ምሕረቱን ፡ አተመ
የፍርድ ፡ አምላክ ፡ ለኃጢአት
ከሰጠ ፡ በቂውን ፡ ቅጣት
መሓሪ ፡ አምላክ
ልጆቹ ፡ አደረገን ፡ በምሕረቱ

ግን ፡ ኢየሱስ ፡ ሆይ! ክልረዳኸን
እንዴት ፡ ደካሞች ፡ እኛ ፡ ነን?
ልጅነታችን ፡ በቀላል
ከእኛ ፡ ይጠፋብናል
የአምላክ ፡ ልጆች ፡ ያደረግኸን
ኦ! ኢየሱስ ፡ አንተ ፡ ጠብቀን

አትራቅብን ፡ ኢየሱስ ፡ ሆይ!
ሁልጊዜ ፡ ከእኛ ፡ ዘንድ ፡ ቆይ
በፈተና ፡ አበርትተህ
በትግልም ፡ አጠንክረህ
በሕይወቱም ፡ በሞቱም ፡ ጻር
በደምህ ፡ ኃይል ፡ ሁን ፡ ከኛ ፡ ጋር