From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
|
|
ሌሎች ፡ የድሮ ፡ መዝሙሮች (Other Classic Mezmur Lyrics)
|
|
ጠላቶችን ፡ እንድንወድ ፡ ጌታ ፡ አስተማረን
በመስቀል ፡ ተቸንክሮ ፡ ፍቅሩን ፡ ገለጸልን
መልካም ፡ ፍቅር ፡ ኦ! መልካም ፡ ፍቅር
ተወለደ ፡ ሊጠላ ፡ ለእኛ ፡ በመስቀል ፡ ሊሰቀል
የአዳምን ፡ ልጆች ፡ ኃጢአት ፡ በደሙ ፡ ለመክፈል
መድኅኔ ፡ አስተምሮኛል ፡ በፍቅር ፡ እንድመራ
ያዘነን ፡ እንዳጽናና ፡ ላጣው ፡ እንድራራ
ይገባኛል ፡ ልታዘዘው
እርሱ ፡ የእኔን ፡ መከራ ፡ ችሎ ፡ ሞቷልና ፡ ሞቷልና
ይገባኛል ፡ እኔም ፡ ልጓዝ ፡ በእርሱ ፡ ጐዳና
በምድር ፡ የምናያቸው ፡ ሁሉ ፡ ይጠፋሉ
ዕምነት ፡ ተስፋና ፡ ፍቅር ፡ ጸንተው ፡ ይኖራሉ
ጌታ ፡ ያዛል ፡ እንድንዋደድ
ጌታ ፡ ነፍሱን ፡ ለእኛ ፡ እስኪሰጥ ፡ አፍቅሮናል
እርስ ፡ በርሳችን ፡ ልኗደድ ፡ ይገባናል
ምሥጋና ፡ ይገባሃል ፡ ክብር ፡ መድኃኒቴ
በሰማያዊ ፡ ፍቅር ፡ ዳበረ ፡ ሕይወቴ
ሃሌሉያ ፡ ኦ! ለጌታዬ
በለመለመ ፡ መስክ ፡ ኢየሱስ ፡ ይመራኛል ፡ ይመራኛል
በየዕለቱ ፡ የጌታ ፡ ፍቅር ፡ ይታየኛል (፪x)
|