ፍቅሩ ፡ ማርኮኛል (Feqeru Markognal)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፦ አልሰለችም ፡ ሁልጊዜ ፡ ጌታን ፡ እባርከዋለሁ
ምህረቱ ፡ በኔ ፡ ላይ ፡ ነው ፡ ይህን ፡ ተረድቻለሁ (፪x)
ኦ ፡ ፍቅሩ ፡ ማርኮኛል (፪x)
ተማርኬያለሁ ፡ በኢየሱስ ፡ ሰላም ፡ አግኝቻለሁ (፪x)

1. ምህረቱ ፡ እጅግ ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ ቸርነቱ ፡ ወደር ፡ የለው
ዓመት ፡ ዓመት ፡ አይለወጥም ፡ ፍቅሩ ፡ ቋሚ ፡ ሁሌ ፡ ጽኑ ፡ ነው
ውድ ፡ ነው ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ እንደሱ ፡ ያለ ፡ ከየት ፡ አገኛለሁ
በኔ ፡ ላይ ፡ የገለጸውን ፡ መውደዱንም ፡ ተረድቻለሁ

አዝ፦ አልሰለችም ፡ ሁልጊዜ ፡ ጌታን ፡ እባርከዋለሁ
ምህረቱ ፡ በኔ ፡ ላይ ፡ ነው ፡ ይህን ፡ ተረድቻለሁ (፪x)
ኦ ፡ ፍቅሩ ፡ ማርኮኛል (፪x)
ተማርኬያለሁ ፡ በኢየሱስ ፡ ሰላም ፡ አግኝቻለሁ (፪x)

2. የአምላኬን ፡ ጥትናውን ፡ የዋህነቱን ፡ አይቼ
አብሬው ፡ ልኖር ፡ ወሰንኩኝ ፡ ልከተለው ፡ ሁሉንም ፡ ትቼ
ወደሱ ፡ መጥቶ ፡ ማን ፡ አፍሯል ፡ ምስኪኑ ፡ ሰው ፡ ቀን ፡ ወጥቶለታል
ሃዘኑ ፡ ማቁ ፡ ተቀዶ ፡ እምባው ፡ ታብሶለት ፡ ይኖራል

አዝ፦ አልሰለችም ፡ ሁልጊዜ ፡ ጌታን ፡ እባርከዋለሁ
ምህረቱ ፡ በኔ ፡ ላይ ፡ ነው ፡ ይህን ፡ ተረድቻለሁ (፪x)
ኦ ፡ ፍቅሩ ፡ ማርኮኛል (፪x)
ተማርኬያለሁ ፡ በኢየሱስ ፡ ሰላም ፡ አግኝቻለሁ (፪x)

3. ድንቅ ፡ የሆነለት ፡ ይዘምር ፡ አይቆጠብ ፡ ማዳኑን ፡ ያውራ
ብቻውን ፡ ታምር ፡ የሚያደርግ ፡ እንደእግዚአብሔር ፡ የለምና
አንደበቶች ፡ ይከፈቱ ፡ የንጉሡን ፡ ምስጋና ፡ ያውሩ
ሰማይን ፡ ምድርን ፡ ለሰራው ፡ ስዎች ፡ ሁሉ ፡ ክብርን ፡ ይስጡ

አዝ፦ አልሰለችም ፡ ሁልጊዜ ፡ ጌታን ፡ እባርከዋለሁ
ምህረቱ ፡ በኔ ፡ ላይ ፡ ነው ፡ ይህን ፡ ተረድቻለሁ (፪x)
ኦ ፡ ፍቅሩ ፡ ማርኮኛል (፪x)
ተማርኬያለሁ ፡ በኢየሱስ ፡ ሰላም ፡ አግኝቻለሁ (፪x)