From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
|
ሌሎች ፡ የድሮ ፡ መዝሙሮች (Other Classic Mezmur Lyrics)
|
|
አዝ፦ ፍቅርህ ፡ ልዩ ፡ ነው ፡ የእኔ ፡ ጌታ (፬x)
ታሪኬን ፡ ለውጠህ ፡ ሥሜን ፡ ቀየርከው
የአንተን ፡ ሥም ፡ መያዜ ፡ ኢየሱስ ፡ በአንተ ፡ ነው
መልካም ፡ የመዓዛ ፡ ጠረን ፡ ሰጥተኸኛል
አንተን ፡ አንተን ፡ ሸቶ ፡ ሰውን ፡ ይማርካል
አዝ፦ ፍቅርህ ፡ ልዩ ፡ ነው ፡ የእኔ ፡ ጌታ (፬x)
አንድ ፡ ሁለት ፡ አይባል ፡ በቃል ፡ አይገለፅ
ከቶ ፡ ምኔን ፡ ልስጥህ ፡ ለውለታህ ፡ ምላሽ
ጠላትህ ፡ ሳለሁ ፡ እኔን ፡ እንዲሁ ፡ ወደኸኛል
በፍቅርህ ፡ ኃይል ፡ ማርከህ ፡ የአንተ ፡ አድርገኸኛል
አዝ፦ ፍቅርህ ፡ ልዩ ፡ ነው ፡ የእኔ ፡ ጌታ (፬x)
|