ፍቅር ፡ ይዞት (Feqer Yizot)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

1. ፍቅር ፡ ይዞት ፡ ይህ ፡ ቸር ፡ የፍቅር ፡ ጌታ
በበረት ፡ ውስጥ ፡ ስለኔ ፡ ተንገላታ
በፍግ ፡ መሃል ፡ ስለኔ ፡ ማልዷል ፡ በሌት
ፍጥረት ፡ ሁሉ ፡ ስለርሱ ፡ ያድርግ ፡ ሐሴት

ስብራት ፡ የሚያውቅ ፡ ይህ ፡ የሕማም ፡ ሰው
ውስጣዊ ፡ ልቤን ፡ እንዴት ፡ ዳሰሰው
ተንቆም ፡ ቢኖር ፡ በሰው ፡ ተጠልቶ
አልተመለሰም ፡ ሥራውን ፡ ከድቶ

2. እንደ ፡ ጠቦት ፡ በሽላች ፡ ፊት ፡ ዝም ፡ አለ
ሸክማችንን ፡ መድኃኒታችን ፡ ቻለ
አፉን ፡ ሳይከፍት ፡ በጠላቶች ፡ ሳይዘብት
ፍቅርን ፡ ለብሶ ፡ መስቀሉን ፡ አሸከሙት

ጐልጐታን ፡ ወጣ ፡ ሲድህ ፡ ሲቧጥጥ
ምድርም ፡ ሲፍቀው ፡ ገላውን ፡ ሲልጥ
የኀዘን ፡ ቀን ፡ ነው ፡ ሆኖም ፡ የደስታ
እርሱ ፡ ተረግሞ ፡ እኛን ፡ ሲፈታ

3. ዓለም ፡ በሌት ፡ በታላቅ ፡ መዳን ፡ ነቃ
ኃይል ፡ ወጣና ፡ ከዓለም ፡ ንጉሥ ፡ ሲቃ
ነፍሱን ፡ ሰጠ ፡ ይህ ፡ ቅዱስ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ልጅ
ከኃጢአት ፡ እኔን ፡ ፈጽሞ ፡ ሊያድን

በቀትር ፡ ሲጮህ ፡ አባቱን ፡ አጥቶ
ጻድቃን ፡ ጣሰ ፡ ምድር ፡ ተከፍቶ
ሥጋውን ፡ ከፍሎ ፡ ጥልን ፡ ከሻረው
ለምን ፡ ይሸሻል ፡ ሰው ፡ ከፈጣሪው