From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
|
|
ሌሎች ፡ የድሮ ፡ መዝሙሮች (Other Classic Mezmur Lyrics)
|
|
አዝ፦ ፍቅር ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ፡ ፍቅር ፡ ነው
ፍቅር ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ፡ ፍቅር ፡ ነው (፪x)
1. ኃጢአት ፡ አሸፍቶት፡ ጫካ ፡ የገባውን
ፀጋውን ፡ ተገፎ ፡ የተራቆተውን
ወዳለበት ፡ ሂዶ ፡ ድምጹን ፡ ያሰማና
ዳግም ፡ ያቆመዋል ፡ ያለባብስና
አዝ፦ ፍቅር ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ፡ ፍቅር ፡ ነው
ፍቅር ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ፡ ፍቅር ፡ ነው (፪x)
2. የበደሉን ፡ ብዛት ፡ መሸከም ፡ ላቃተው
ነገር ፡ ግራ ፡ ገብቶት ፡ ለሚወተውተው
ፍቅር ፡ ሲጐበኘው ፡ ሲሰጠው ፡ ምልክት
በእርጋታ ፡ ይቀመጣል ፡ ይሆናል ፡ ባለርስት
አዝ፦ ፍቅር ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ፡ ፍቅር ፡ ነው
ፍቅር ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ፡ ፍቅር ፡ ነው (፪x)
3. ወንድሞቹ ፡ ጠልተውት ፡ በጉድጓድ ፡ ለጣሉት
ከሞቀ ፡ ሠልፉ ፡ በግፍ ፡ ላባረሩት
አፍቃሪው ፡ እግዚአብሔር ፡ አብሮት ፡ ይወጣና
ሰባሳቢ ፡ ያደርገዋል ፡ ሥፍራ ፡ ይሰጠውና
አዝ፦ ፍቅር ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ፡ ፍቅር ፡ ነው
ፍቅር ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ፡ ፍቅር ፡ ነው (፪x)
4. በትልቅ ፡ ዋሻ ፡ ውስጥ ፡ ወስደው ፡ ለቀበሩት
ድንጋይ ፡ ገጥመውበት ፡ አከተመ ፡ ላሉት
በሐዘኑ ፡ ሰፈር ፡ ፍቅር ፡ ፈጥኖ ፡ ደርሶ
ወገን ፡ ያደርገዋል ፡ ሟቹን ፡ አስነስቶ
አዝ፦ ፍቅር ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ፡ ፍቅር ፡ ነው
ፍቅር ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ፡ ፍቅር ፡ ነው (፪x)
5. ዓለሙን ፡ በሙሉ ፡ እንዲሁ ፡ የወደደ
በክርስቶስ ፡ በኩል ፡ ጥልን ፡ ያስወገደ
ፍፁም ፡ ቅዱስና ፡ ርህሩህ ፡ የሆነው
ዘመን ፡ የማይሽረው ፡ እግዚአብሔር ፡ ፍቅር ፡ ነው
አዝ፦ ፍቅር ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ፡ ፍቅር ፡ ነው
ፍቅር ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ፡ ፍቅር ፡ ነው (፪x)
|