ፍቅር ፡ ኢየሱስ ፡ ነው (Feqer Eyesus New)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፦ ፍቅር ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ፍቅር
የፍቅርን ፡ ትርጉም ፡ ያጣ ፡ ሰው
ወደ ፡ ኢየሱስ ፡ መጥቶ ፡ ይቅሰመው
እኛስ ፡ የፍቅር ፡ ልጆች ፡ ነን
ከፍቅሩ ፡ እንጀራ ፡ እንቀምሳለን

1. ፍቅር ፡ ሰማርያ ፡ ወረደ
ከጉድጓድ ፡ አፍ ፡ ላይ ፡ ቆመ
አንዲት ፡ ሴት ፡ ልትቀዳ ፡ ውኃ
መጣች ፡ እንስራዋን ፡ ይዛ
የልቧን ፡ ሁሉ ፡ ነገራት
እንቆቅልሿን ፡ ፈታላት
ፍቅር ፡ ሰማርያ ፡ ገብቶ
አሸነፈ ፡ ወንጌል ፡ ዘርቶ

አዝ፦ ፍቅር ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ፍቅር
የፍቅርን ፡ ትርጉም ፡ ያጣ ፡ ሰው
ወደ ፡ ኢየሱስ ፡ መጥቶ ፡ ይቅሰመው
እኛስ ፡ የፍቅር ፡ ልጆች ፡ ነን
ከፍቅሩ ፡ እንጀራ ፡ እንቀምሳለን

2. ፍቅር ፡ ወደ ፡ ቃና ፡ ሄደ
ለሠርግ ፡ ገሊላ ፡ ታደለ
ግን ፡ የወይኑ ፡ ጠጅ ፡ አለቀ
ጋኑ ፡ ብቻ ፡ ባዶ ፡ ቀረ
ተጋባዡ ፡ ፍቅር ፡ ተነስቶ
ውኃ ወደ ፡ ወይን ፡ ቀይሮ
ፍቅር ፡ ፈጥኖ ፡ ረዳቸው
ከውርደት ፡ ከአፍረት ፡ አዳናቸው

አዝ፦ ፍቅር ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ፍቅር
የፍቅርን ፡ ትርጉም ፡ ያጣ ፡ ሰው
ወደ ፡ ኢየሱስ ፡ መጥቶ ፡ ይቅሰመው
እኛስ ፡ የፍቅር ፡ ልጆች ፡ ነን
ከፍቅሩ ፡ እንጀራ ፡ እንቀምሳለን

3. ፍቅር ፡ ዘኪዮስ ፡ ቤት ፡ ገባ
ቀራጩ ፡ ቤት ፡ ምሳ ፡ በላ
ፍቅር ፡ ሁሉን ፡ ሰው ፡ ይወዳል
ከሾላ ፡ ዛፍ ፡ ላይ ፡ አውርዶ
ቤቱ ፡ ገባ ፡ ተከትሎ
የዘኪዮስ ፡ ቤት ፡ ዳነ
የኃጢአት ፡ ዕዳው ፡ ተከፈለ

አዝ፦ ፍቅር ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ፍቅር
የፍቅርን ፡ ትርጉም ፡ ያጣ ፡ ሰው
ወደ ፡ ኢየሱስ ፡ መጥቶ ፡ ይቅሰመው
እኛስ ፡ የፍቅር ፡ ልጆች ፡ ነን
ከፍቅሩ ፡ እንጀራ ፡ እንቀምሳለን

4. አመንዝራዋን ፡ ሊወግራት
ፍቅር ፡ ካለው ፡ ዘን ፡ ለፍርድ ፡ አመጧት
ፍቅር ፡ ስለ ፡ እሷ ፡ ፈረደ
ካጠገቧ ፡ ሁሉም ፡ ሸሸ
ደግመሽ ፡ አትስሪ ፡ አለና
ፍቅር ፡ ሸኛት ፡ በይቅርታ
አዳናት ፡ ፍቅር ፡ ከድንጋይ
ዘለዓለም ፡ ይክበር ፡ በሠማይ

አዝ፦ ፍቅር ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ፍቅር
የፍቅርን ፡ ትርጉም ፡ ያጣ ፡ ሰው
ወደ ፡ ኢየሱስ ፡ መጥቶ ፡ ይቅሰመው
እኛስ ፡ የፍቅር ፡ ልጆች ፡ ነን
ከፍቅሩ ፡ እንጀራ ፡ እንቀምሳለን

5. ጴጥሮስ ፡ ኢየሱስን ፡ ካደ
በገረድ ፡ ፊት ፡ ተሳደበ
ግን ፡ ዶሮ ፡ ሲጮህ ፡ አስታወሰ
ምርር ፡ ብሎ ፡ አልቅሶ
የፍቅርን ፡ ቃል ፡ አስቦ
ፍቅርን ፡ ይቅርታ ፡ ለምኖ
ፍቅርም ፡ ሳበው ፡ ወደ ፡ ቤቱ
አለት ፡ አደረገው ፡ ለቤቱ

አዝ፦ ፍቅር ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ፍቅር
የፍቅርን ፡ ትርጉም ፡ ያጣ ፡ ሰው
ወደ ፡ ኢየሱስ ፡ መጥቶ ፡ ይቅሰመው
እኛስ ፡ የፍቅር ፡ ልጆች ፡ ነን
ከፍቅሩ ፡ እንጀራ ፡ እንቀምሳለን

6. ፍቅር ፡ እስረኛን ፡ ያስፈታል
ኃጢአተኛን ፡ ነጻ ፡ ያወጣል
በርባንም ፡ ወንበዴ ፡ ሰው ፡ ነበረ
 የታሰረ : ለመገደል
ስለ ፡ በደለ ፡ አይሁድን
ሲጠባበቅ ፡ ነበረ ፡ ፍርድን
ግን ፡ ፍቅር ፡ በመሃል ፡ ገባ
በርባን ፡ በነጻ ፡ ተፈታ

አዝ፦ ፍቅር ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ፍቅር
የፍቅርን ፡ ትርጉም ፡ ያጣ ፡ ሰው
ወደ ፡ ኢየሱስ ፡ መጥቶ ፡ ይቅሰመው
እኛስ ፡ የፍቅር ፡ ልጆች ፡ ነን
ከፍቅሩ ፡ እንጀራ ፡ እንቀምሳለን