ፍቅር ፡ ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነው (Feqer Eyesus Becha New)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

1. የሚወደውን ፡ ማን ፡ ይጠላል
እንስሳም ፡ ወገኑን ፡ ይወዳል
ፍቅር ፡ ግን ፡ እስከ ፡ ሞት ፡ ጥልቅ ፡ ናት
የለችም ፡ የትም ፡ ብንፈልጋት

አዝ፦ ፍቅር ፡ ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነው
እስከሞት ፡ ድረስ ፡ የታመነው
አየነው ፡ ሁሉንም ፡ አየነው (፪x)
ፍቅር ፡ እግዚአብሔር ፡ ብቻ ፡ ነው

2. ምክንያት ፡ ሲኖር ፡ ለመውደድ
ወዳጁ ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ የሚያደርግ
ችግር ፡ ሲመጣ ፡ መመረሩ
ይጠፋል ፡ ያኔ ፡ ወረት ፡ ፍቅሩ

አዝ፦ ፍቅር ፡ ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነው
እስከሞት ፡ ድረስ ፡ የታመነው
አየነው ፡ ሁሉንም ፡ አየነው (፪x)
ፍቅር ፡ እግዚአብሔር ፡ ብቻ ፡ ነው

3. ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ግን ፡ ፍቅር ፡ አለው
የመስቀል ፡ ሞት ፡ እንኳን ፡ ያላገደው
ምንም ፡ ሳይሻ ፡ ከእኛ
ተጐሳቆለ ፡ ስለ ፡ እኛ

አዝ፦ ፍቅር ፡ ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነው
እስከሞት ፡ ድረስ ፡ የታመነው
አየነው ፡ ሁሉንም ፡ አየነው (፪x)
ፍቅር ፡ እግዚአብሔር ፡ ብቻ ፡ ነው

4. ስለወደደን ፡ ከአንጀቱ
ስለእኛ ፡ ሰጠ ፡ ሕይወቱን
ከቶ ፡ ፍቅር ፡ የለም ፡ ከእርሱ ፡ ሌላ
ወረት ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ ሽንገላ

አዝ፦ ፍቅር ፡ ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነው
እስከሞት ፡ ድረስ ፡ የታመነው
አየነው ፡ ሁሉንም ፡ አየነው (፪x)
ፍቅር ፡ እግዚአብሔር ፡ ብቻ ፡ ነው