ፈቃድህን ፡ አድርግ (Feqadehen Adreg)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ፈቃድህን ፡ አድርግ ፡ ኦ ! ጌታ ፡ ሆይ
አንተ ፡ መሪ ፡ ነህ ፡ እኔ ፡ ሸክላ
አብጀኝ ፡ ሥራኝ ፡ እንደምትወድ
ስጠብቅህ ፡ ሳለ ፡ በፈቃዴ

ፈቃድህን ፡ አድርግ ፡ ኦ ! ጌታ ፡ ሆይ
መርምረኝ ፡ እየኝ ፡ ጌታ ፡ ዛሬ
እንደ ፡ በረዶ ፡ አንጻኝ ፡ አሁን
በፊትህ ፡ ስቀርብ ፡ ትሁት ፡ ልሁን

ፈቃድህን ፡ አድርግ ፡ ኦ ! ጌታ ፡ ሆይ
መርምረኝ ፡ እና ፡ እርዳኝ ፡ ጌታ
ኃይልና ፡ ችሎት ፡ የአንተ ፡ ናቸው
ዳሰኝ ፡ ፈውሰኝ ፡ መድሃኒቴ

ፈቃድህን ፡ አድርግ ፡ ኦ ! ጌታ ፡ ሆይ
መርምረኝ ፡ ግዛ ፡ ሰውነቴን
በመንፈስ ፡ ሙላኝ ፡ ሁሉ ፡ እስኪያይ
አንተ ፡ መኖርህን ፡ በሕይወቴ