እዘምራለሁ ፡ እዘምራለሁ (Ezemeralehu Ezemeralehu)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

በሕይወቴ ፡ ድንቅ ፡ ለውጥ ፡ ሆነ
ከኢየሱስ ፡ ጋር ፡ ስኖር
ከእንግዲህ ፡ አልጨነቅም
ስለሚንከባከበኝ

አዝ፦ እዘምራለሁ ፡ እዘምራለሁ
ለኢየሱስ ፡ ለሞተልኝ
እዘምራለሁ ፡ እዘምራለሁ
እስከ ፡ ዘለዓለሙ

ሕይወቴ ፡ በኃጢአት ፡ ሞልቶ
በችግር ፡ ስኖር ፡ ሳለሁ
ግን ፡ ኢየሱሴ ፡ መጥቶ ፡ ረዳኝ
ችግሬም ፡ ሁሉ ፡ ራቀ

አዝ፦ እዘምራለሁ ፡ እዘምራለሁ
ለኢየሱስ ፡ ለሞተልኝ
እዘምራለሁ ፡ እዘምራለሁ
እስከ ፡ ዘለዓለሙ

ብዙ ፡ መሰናክል ፡ አለ
ኢየሱስን ፡ ስከተል
ግን ፡ ረዳቴና ፡ ብርታቴ ፡ ኢየሱስ
ክርስቶስ ፡ ብቻ ፡ ነው

አዝ፦ እዘምራለሁ ፡ እዘምራለሁ
ለኢየሱስ ፡ ለሞተልኝ
እዘምራለሁ ፡ እዘምራለሁ
እስከ ፡ ዘለዓለሙ

ሌላ ፡ መንገድ ፡ አልሞክርም
ተስፋ ፡ የለውምና
የጌታ ፡ የኢየሱስ ፡ መንገድ ፡ ግን
ተስፋና ፡ ደስታ ፡ አለው

አዝ፦ እዘምራለሁ ፡ እዘምራለሁ
ለኢየሱስ ፡ ለሞተልኝ
እዘምራለሁ ፡ እዘምራለሁ
እስከ ፡ ዘለዓለሙ