ኢየሱስን ፡ ያስፈልገኛል (Eyesusen Yasfelegegnal)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ኢየሱስን ፡ ያስፈልገኛል
በደሌን ፡ ይቅር ፡ ይላል
ጋሻም ፡ ይሆንልኛል
እርሱ ፡ ብቻ ፡ ያድነኛል
ፍቅሩም ፡ ሕይወት ፡ ነው ፡ ለእኔ
ኢየሱስ ፡ ነው ፡ መድኃኒቴ

ያለ ፡ ኢየሱስ ፡ ተስፋም ፡ የለኝ
ያለ ፡ ኢየሱስ ፡ ምሕረትም
ምንም ፡ አይሆንልኝም
ኢየሱስ ፡ ዕምነትን ፡ ካሰጠኝ
አላገኝም ፡ ለፍቼ
ኢየሱስ ፡ ነው ፡ መድኃኒቴ

ስለዚህ ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ ኢየሱስ
እመጣለሁ ፡ ለምኜ
ፀጋህን ፡ ተማጥኜ
ዕውነተኛውን ፡ ሕይወት ፡ ለኩስ
በተሰበረው ፡ ልቤ
አንተ ፡ ነህ ፡ መድኃኒቴ