ኢየሱስን ፡ ትቼ ፡ ዓለምን ፡ ባተርፍ (Eyesusen Techie Alemen Baterf)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ኢየሱስን ፡ ትቼ ፡ ዓለምን ፡ ባተርፍ
የዕለት ፡ ሕይወቴ ፡ ጥቅመ ፡ ቢስ ፡ ነው
በሐብቴ ፡ ብዛት ፡ ዕረፍት ፡ የለኝም
ልቤም ፡ ሰላምን ፡ አያገኝም
ኢየሱሴን ፡ ትቼ ፡ ዓለምን ፡ ባተርፍ
ጥረቴ ፡ ሁሉ ፡ አይረባኝም
ይልቅ ፡ ኢየሱስን ፡ የእኔ ፡ ባደርገው
ለልቤ ፡ ሰላም ፡ አገኛለሁ

ሰዎች ፡ ቢያፈቅሩኝ ፡ ሐብቴም ፡ ቢበዛ
ስሜንም ፡ ደግሞ ፡ ቢያከብሩልኝ
ተስፋም ፡ ባይኖረኝ ፡ ልሠራ ፡ ወደብ ፡ ተጉዤ
ሄጄ ፡ የት ፡ ላርፍ ፡ ነኝ?
ኢየሱሴን ፡ ብክድ ፡ የሞተልኝን
መስቀሉን ፡ ብጥል ፡ ያዝ ፡ ያለኝን
ጌታ ፡ ሲገለጽ ፡ በአሰቃቂው ፡ ቀን
ማንም ፡ አይችልም ፡ እኔን ፡ ሊያድን

አልችልም ፡ እኔ ፡ ልኖር ፡ ብቻዬን
ያለ ፡ ኢየሱሴ ፡ በዚች ፡ ዓለም ፡ መንገዴ
ያለ ፡ እርሱ ፡ ይጨልማል
ልቤም ፡ በሐዘን ፡ ይጨነቃል
ብኖርስ ፡ እንኳ ፡ ያለ ፡ መድህኔ
በጠራኝ ፡ ጊዜ ፡ ምን ፡ ይዋጠኝ ?
በሌላ ፡ መንገድ ፡ ልሄድ ፡ ብሞክር
ሕይወት ፡ የለኝም ፡ ለዘለዓለም

የኢየሱስ ፡ መሆን ፡ ታላቅ ፡ ደስታ ፡ ነው
ልብን ፡ የሚፈውስ ፡ ቸር ፡ አዳኝ ፡ ነው ፡
ኃጥያቴን ፡ ሁሉ ፡ ይቅር ፡ ይለኛል
ልቤን ፡ በደሙ ፡ ያጥብልኛል
ኢየሱስን ፡ ብይዝ ፡ ኢየሱሴን ፡ ብቻ
ምን ፡ ባልፈልግ ፡ ከእርሱ ፡ ሌላ
የሚያስፈልገኝን ፡ ይሰጠኛል
ለዘለዓለም ፡ ይጠብቀኛል