ኢየሱስን ፡ እንደሰው ፡ አትጠራጠረው (Eyesusen Endesew Ateteraterew)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ከጠላት ፡ ፍላጻ ፡ ከሰይፍ ፡ ያድንሃል
በረሃብም ፡ ዘመን ፡ ከሞት ፡ ያስጥልሃል
ስሙን ፡ ያስከብራል ፡ ቁም ፡ ነገርን ፡ ያውቃል
ህጻን ፡ ስላይደለ ፡ ያለውን ፡ ይፈጽማል

አዝ፦ ኢየሱስን ፡ እንደ ፡ ሰው ፡ አትጠራጠረው
መዋሸት ፡ አያውቅም ፡ ተስፋህን ፡ ጠብቀው
አይጥልህምና ፡ በመከራ ፡ ጥራው
አፍህ ፡ እያመነው ፡ በልብህ ፡ አትክዳው

ለታማኝነቱ ፡ ተው ፡ ገደብ ፡ አትስጠው
ለወላዋይ ፡ ልብህ ፡ ጽናት ፡ አትንፈገው
የዘለዓለም ፡ አምላክ ፡ እግዚአብሔር ፡ አይዋሽም
የገባልህን ፡ ቃል ፡ ፈጽሞ ፡ አይክድም

አዝ፦ ኢየሱስን ፡ እንደ ፡ ሰው ፡ አትጠራጠረው
መዋሸት ፡ አያውቅም ፡ ተስፋህን ፡ ጠብቀው
አይጥልህምና ፡ በመከራ ፡ ጥራው
አፍህ ፡ እያመነው ፡ በልብህ ፡ አትክዳው

ከእርሱ ፡ ጋር ፡ ከሆንክ ፡ ከአንተ ፡ ጋራ ፡ ነው
አውጥቶ ፡ እንዳይጥልህ ፡ ብቻ ፡ አትተወው
አስብ ፡ ቆም ፡ ብለህ ፡ ያለፍከውን ፡ ዘመን
ዛሬም ፡ አምነህ ፡ ጥራው ፡ ያኔ ፡ ያዳነህን

አዝ፦ ኢየሱስን ፡ እንደ ፡ ሰው ፡ አትጠራጠረው
መዋሸት ፡ አያውቅም ፡ ተስፋህን ፡ ጠብቀው
አይጥልህምና ፡ በመከራ ፡ ጥራው
አፍህ ፡ እያመነው ፡ በልብህ ፡ አትክዳው

ስሙን ፡ እየጠራህ ፡ ስንቱን ፡ አምልጠሃል
ከስንቱስ ፡ አደጋ ፡ ስንት ፡ ጊዜ ፡ ድነሃል
ውለታውን ፡ ሲረሱ ፡ ጌታ ፡ ቅር ፡ ይለዋል
በቃሉ ፡ ብታምን ፡ ሁሉ ፡ ይቻልሃል

አዝ፦ ኢየሱስን ፡ እንደ ፡ ሰው ፡ አትጠራጠረው
መዋሸት ፡ አያውቅም ፡ ተስፋህን ፡ ጠብቀው
አይጥልህምና ፡ በመከራ ፡ ጥራው
አፍህ ፡ እያመነው ፡ በልብህ ፡ አትክዳው