ኢየሱስ ፡ ይጠራሃል (Eyesus Yeterahal)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ኢየሱስ ፡ በገርነት ፡ ይጠራሃል
ዛሬውኑ ፡ ይጠራሃል
ስለምንስ ፡ ከሚያበራው ፡ ፍቅር
በጣሙን ፡ ትርቃለህ?

አዝማች
ዛሬውኑ ፡ ይጠራሃል
ኢየሱስ ፡ ይጠራሃል
በለዘብታ ፡ ይጠራሃል

ኢየሱስ ፡ ደካማን ፡ እንዲያርፍ ፡ ይጠራል
ዛሬውኑ ፡ ይጠራናል
ሸክምህን ፡ አምጣ ፡ እንድትባረክ
እርሱም ፡ አያባርህም

አዝማች
ዛሬውኑ ፡ ይጠራሃል
ኢየሱስ ፡ ይጠራሃል
በለዘብታ ፡ ይጠራሃል

ኢየሱስ ፡ ይጠራሃል
ና ፡ ወደርሱ ፡ ዛሬውኑ
ይጠብቃል ፡ ክነኃጢአትህ
መጥተህ ፡ ተንበርከክ
ና ፡ እንግዲህ ፡ አትዘግይ

አዝማች
ዛሬውኑ ፡ ይጠራሃል
ኢየሱስ ፡ ይጠራሃል
በለዘብታ ፡ ይጠራሃል

ኢየሱስ ፡ ይጠራል
ጥሪውን ፡ ስማ ፡ ዛሬ
ዛሬ ፡ ስማው
ስሙን ፡ ያመኑ ፡ ይደሰታሉ
ተነሡ ፡ እንቅረበው

አዝማች
ዛሬውኑ ፡ ይጠራሃል
ኢየሱስ ፡ ይጠራሃል
በለዘብታ ፡ ይጠራሃል