ኢየሱስ ፡ የሳሮን ፡ ጽጌረዳ (Eyesus Yesaron Tsegiereda)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ምስኪን ፡ ሲጮህ ፡ በጨለማ
ወይ ፡ የሚል ፡ አጥቶ ፡ የሚሰማ
ትንፋሽ ፡ አጥቶ ፡ ጣር ፡ ሲይዘው
ትደርሳለህ ፡ ልትረዳው (፫x)

አዝ፦ ኢየሱስ ፡ የሳሮን ፡ ጽጌረዳ ፤ የውስጥ ፡ የልብን ፡ የምትረዳ
የተሰወረን ፡ ትገልጣለህ ፤ መዝሙር ፡ በሌሊት ፡ ትሰጣለህ
ከጌጥም ፡ በላይ ፡ ጌጥ ፡ ነህ
ከወርቅ ፡ ከዕንቁ ፡ ትበልጣለህ (፫x)

ክፉው ፡ አይሎ ፡ እጅ ፡ እግር ፡ ሲያስር
ሲያሰናዳ ፡ ለመቃብር
የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ
ሞትን ፡ የሚጥል ፡ ቃልም ፡ አለህ (፫x)

አዝ፦ ኢየሱስ ፡ የሳሮን ፡ ጽጌረዳ ፤ የውስጥ ፡ የልብን ፡ የምትረዳ
የተሰወረን ፡ ትገልጣለህ ፤ መዝሙር ፡ በሌሊት ፡ ትሰጣለህ
ከጌጥም ፡ በላይ ፡ ጌጥ ፡ ነህ
ከወርቅ ፡ ከዕንቁ ፡ ትበልጣለህ (፫x)

ስምህ ፡ እንደሚፈስ ፡ ዘይት ፡ ነው
ለተጐዳው ፡ ለቆሰለው
ውስጥ ፡ አዋቂ ፡ የልብ ፡ ወዳጅ
ለሁልጊዜ ፡ የምትመች (፫x)

አዝ፦ ኢየሱስ ፡ የሳሮን ፡ ጽጌረዳ ፤ የውስጥ ፡ የልብን ፡ የምትረዳ
የተሰወረን ፡ ትገልጣለህ ፤ መዝሙር ፡ በሌሊት ፡ ትሰጣለህ
ከጌጥም ፡ በላይ ፡ ጌጥ ፡ ነህ
ከወርቅ ፡ ከዕንቁ ፡ ትበልጣለህ (፫x)

ከጥላህ ፡ ስር ፡ ለሚኖሩ
በአንተ ፡ ፍቅር ፡ ለታሰሩ
ለጉሮሮ ፡ ፍሬ ፡ ጣፋጭ
መዓዛህ ፡ መልካም ፡ የማትሰለች (፫x)

አዝ፦ ኢየሱስ ፡ የሳሮን ፡ ጽጌረዳ ፤ የውስጥ ፡ የልብን ፡ የምትረዳ
የተሰወረን ፡ ትገልጣለህ ፤ መዝሙር ፡ በሌሊት ፡ ትሰጣለህ
ከጌጥም ፡ በላይ ፡ ጌጥ ፡ ነህ
ከወርቅ ፡ ከዕንቁ ፡ ትበልጣለህ (፫x)

ደናግሎች ፡ አንተን ፡ ወደው
ተከተሉህ ፡ ሁሉን ፡ ትተው
ስላወቁ ፡ ማጽናናትህን
ከወርቅ ፡ ከዕንቁ ፡ መብለጥህን (፫x)

አዝ፦ ኢየሱስ ፡ የሳሮን ፡ ጽጌረዳ ፤ የውስጥ ፡ የልብን ፡ የምትረዳ
የተሰወረን ፡ ትገልጣለህ ፤ መዝሙር ፡ በሌሊት ፡ ትሰጣለህ
ከጌጥም ፡ በላይ ፡ ጌጥ ፡ ነህ
ከወርቅ ፡ ከዕንቁ ፡ ትበልጣለህ (፫x)