ኢየሱስ ፡ የምር ፡ ወዳጄ ፡ ነው (Eyesus Yemer Wedajie New)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ኢየሱስ ፡ የምር ፡ ወዳጄ ፡ ነው
ተስፋዬ ፡ ሕይወቴም
ብርታቴ ፡ ነው ፡ በየቀኑ
ያለ ፡ እርሱ ፡ እወድቃለሁ
ባዘንኩ ፡ ጊዜ ፡ ይቀርበኛል
መጽናናትም ፡ ይሰጠኛል
ባዘንኩ ፡ ጊዜ ፡ ደስታዬ ፡ ነው
ወ ዳ ጄ

ኢየሱስ ፡ የምር ፡ ወዳጄ ፡ ነው
በችግር ፡ ረዳቴ
በረከትን ፡ ከእርሱ ፡ እሻለሁ
እርሱም ፡ ይሰጠኛል
ዝናብ ፡ ፀሐይን ፡ ይልካል
ደግሞም ፡ ወርቃዊ ፡ አዝመራ
በረከቱን ፡ ይሰጠኛል ፡ ወዳጄ

ኢየሱስ ፡ የምር ፡ ወዳጄ ፡ ነው
ታማኙ ፡ እሆናለሁ
እርሱም ፡ ለእኔ ፡ ታማኜ ፡ ነው
እንዴት ፡ እክደዋለሁ?
እከተል ፡ ዘንድ ፡ ይገባኛል
በሌት ፡ በቀን ፡ ይመራኛል
መከተል ፡ ነው ፡ ቀንና ፡ ሌት
ወ ዳ ጄ

ኢየሱስ ፡ የምር ፡ ወዳጄ ፡ ነው
ሌላም ፡ አያሻኝም
አምነዋለሁ ፡ ዓለም ፡ እስኪያልፍ
አሁንም ፡ አምነዋለሁ
ከእርሱ ፡ ጋር ፡ መኖር ፡ ውብ ፡ ነው
ደግሞም ፡ ፍጻሜ ፡ የለውም
የዘለዓለም ፡ ደስታ ፡ ሕይወት
ወ ዳ ጄ