የሱስ ፡ የልቤ ፡ ወዳጅ (Eyesus Yelebie Wedaj)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

የሱስ ፡ የልቤ ፡ ወዳጅ
ወደ ፡ አንተ ፡ አስጠጋኝ
መከራ ፡ ሲመጣብኝ
ሞገዱ ፡ ሲነሣብኝ
ሸሽገኝ ፡ ልኡል ፡ አምላክ
የሕይወት ፡ ችግር ፡ እስኪያልፍ
ወደ ፡ ሰማይ ፡ አድርሰኝ
ነፍሴንም ፡ ተቀበላት

ያለአንተ ፡ ጥግ ፡ የለኝም
በአንተ ፡ ታምኛለሁ
ብቻዬን ፡ አትተወኝ
አጽናናኝ ፡ ተሸከመኝ
እታመንብሃለሁ
እርዳታህን ፡ እሻለሁ
ደካማ ፡ ሰውነቴን
በፍቅርህ ፡ እኔን ፡ ጋርደኝ

በአንተ ፡ ብቻ ፡ ከታመንሁ
ሁሉንም ፡ አገኛለሁ
ደግፍ ፡ የደከሙትን
ፈውስ ፡ የታመሙትን
አንተ ፡ ዕውነተኛ ፡ ነህ
እኔ ፡ ግን ፡ ያልነጻሁ ፡ ነኝ
በኃጢአት ፡ የተሞላሁ
አንተ ፡ ታነጻኛለህ

በፀጋ ፡ የተሞላህ
ለሃጥያት ፡ ይቅርታ ፡ ሰጭ
ሃጥያቴን ፡ አስወግደህ
ና ፡ በንጽሕና ፡ ያዘኝ
አንተ ፡ የሕይወት ፡ ምንጭ ፡ ነህ
በነፃ ፡ ልቀበልህ
በልቤ ፡ ውስጥም ፡ ፍለቅ
ለዘለዓለም ፡ ኑርልኝ