ኢየሱስ ፡ ያውቃል (Eyesus Yawqal)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ኢየሱስ ፡ ያውቃል
ልቤ ፡ ሲጨነቅ
ደስታና ፡ መዝሙር ፡ ስናፍቅ
ሸክም ፡ ሲበዛ
ደግሞም ፡ ስጨነቅ
ደክሞኝ ፡ ታክቶኝ
ጉዞው ፡ ሲርቅ

አዝ፦ አዎን ፡ ያውቃል ፡ ይጨነቃል
ሳዝን ፡ ልቡ ፡ ይነካል
ጊዜያቱ ፡ ሲያደክመኝ
ሌቱም ፡ ሲያታክተኝ
መድኃኒቴ ፡ ያውቃል (፪x)

ኢየሱስ ፡ ያውቃል
ሲጨልምብኝ
ድንጋጤ ፡ ፍርሃት ፡ ሲይዘኝ
ቀኑ ፡ ሲያበቃ
ብርኃን ፡ ሲጨልም
ያውቀኛል ፡ ወይ?
እንዲቀርበኝ

አዝ፦ አዎን ፡ ያውቃል ፡ ይጨነቃል
ሳዝን ፡ ልቡ ፡ ይነካል
ጊዜያቱ ፡ ሲያደክመኝ
ሌቱም ፡ ሲያታክተኝ
መድኃኒቴ ፡ ያውቃል (፪x)

ያውቀኛል ፡ ወይ?
ፈተና ፡ ስወድቅ
በፈተና ፡ እንድዘልቅ
ለኃዘኔ ፡ ጥልቅ ፡ ረዳቴ ፡ ሲርቅ
በሌት ፡ እንባዬ ፡ ሲጥለቀለቅ

አዝ፦ አዎን ፡ ያውቃል ፡ ይጨነቃል
ሳዝን ፡ ልቡ ፡ ይነካል
ጊዜያቱ ፡ ሲያደክመኝ
ሌቱም ፡ ሲያታክተኝ
መድኃኒቴ ፡ ያውቃል (፪x)

ያየኛል ፡ ወይ?
ስሰናበት ፡ ከዘመድ ፡ ከእናት ፡ ከአባት
ልቤ ፡ ሲቆስል ፡ በኃዘን ፡ ብዛት
ያውቃል ፡ ወይ?
የሰማይ ፡ አባት

አዝ፦ አዎን ፡ ያውቃል ፡ ይጨነቃል
ሳዝን ፡ ልቡ ፡ ይነካል
ጊዜያቱ ፡ ሲያደክመኝ
ሌቱም ፡ ሲያታክተኝ
መድኃኒቴ ፡ ያውቃል (፪x)