ኢየሱስ ፡ ያስፈልገኛል (Eyesus Yasfelegegnal)
From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
|
ሌሎች ፡ የድሮ ፡ መዝሙሮች (Other Classic Mezmur Lyrics)
|
|
ኢየሱስ ፡ ያስፈልገኛል
በደሌን ፡ ይቅር ፡ ይላል
ጋሻም ፡ ይሆንልኛል
እርሱ ፡ ብቻ ፡ ያድነኛል
ፍቅሩም ፡ ሕይወት ፡ ነው ፡ ለእኔ
ኢየሱስ ፡ ነው ፡ መድኃኒቴ
ያለ ፡ ኢየሱስ ፡ ተስፋም ፡ የለኝ
ያለ ፡ ኢየሱስ ፡ ምሕረትም
ምንም ፡ አይሆንልኝም
ኢየሱስ ፡ ዕምነትን ፡ ካልሰጠኝ
አላገኝም ፡ ለፍቼ
ኢየሱስ ፡ ነው ፡ መድኃኒቴ
ስለዚህ ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ ኢየሱስ
እመጣለሁ ፡ ለምኜ
ፀጋህን ፡ ተማጥኜ
ዕውነተኛውን ፡ ሕይወት ፡ ለኩስ
በተሰበረው ፡ ልቤ
አንተ ፡ ነህ ፡ መድኃኒቴ
|