ኢየሱስ ፡ ወደሄድክበት (Eyesus Wedehiedkebet)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ኢየሱስ ፡ ወደሄድክበት
ናፍቆት ፡ ተነሣብኝ
አይገኝም ፡ ሕይወት ፡ ዕረፍት
ዓለም ፡ በሚሰጠኝ
ሃሣቤን ፡ የሚቀድስ
ልቤን ፡ የሚያድስ
አውርድልኝ ፡ መንፈስህን
ፀጋን ፡ አፍስስልኝ

ፈተናን ፡ ለማሸነፍ
ክፉን ፡ ድል ፡ ለመንሣት
እኔን ፡ በኃይልህ ፡ ደግፍ
ጠብቀኝ ፡ ከኃጢአት
ከጥፋት ፡ ልታድነኝ
ወደህ ፡ የሞትክልኝ
በዳገት ፡ ወይስ ፡ በድልድል
ደስ ፡ ብሎኝ ፡ ልከተል

ከኃጢአት ፡ ተለይቼ
ጻድቅ ፡ ልሆንልህ
ቅዱስ ፡ ማጽርያ ፡ ለእኔ
አቅርበህ ፡ በደምህ
በሰማይ ፡ ዕድል ፡ ላገኝ
መግባት ፡ ሊሆንልኝ
ከመቅብር ፡ ተነሣህ
ገብተሃል ፡ በግርማህ

ብጹዕ ፡ ለመሆን ፡ ልመኝ
ከፍ ፡ ልል ፡ ከከንቱነት
በቸርነት ፡ ጠራኸኝኝ
ለዘለዓለም ፡ ሕይወት
ከዚህ ፡ ምድራዊ ፡ ውርደት
ሽቅብ ፡ ልመለከት
ወደዚያ ፡ ለመግባት
ለደራጅ ፡ በትጋት

ደግሞ ፡ እንዳይደልለኝ
ጠብቀኝ ፡ ከዓለም
ከክፉ ፡ ምኞት ፡ ለየኝ
ሕግህን ፡ ልፈጽም
በኪዳንህ ፡ ልጠበቅ
ፀጋህን ፡ አስታውቅ
ነፍሴን ፡ በብሩክ ፡ ስንብቻ
እስከምትጠራ