ኢየሱስ ፡ ሲጠራህ ፡ ወደ ፡ ሰማይ (Eyesus Siterah Wede Semay)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ኢየሱስ ፡ ሲጠራህ ፡ ወደ ፡ ሰማይ
ቸኩል ፡ ወደርሱ ፡ ሳትዘገይ
መንገዱንም ፡ ያስተምርሃል
ፍቅሩም ፡ ይታይሃል
ምን ፡ ይሆናል ፡ ለሰማይ ፡ መናኝ
ድኖ ፡ ከአምላክ ፡ ጋራ ፡ ሲገናኝ
ምን ፡ ያህል ፡ ደስታ ፡ አለ ፡ በላይ
በቤቱ ፡ በሰማይ

ዛሬም ፡ በቃሉ ፡ ቀርቦልሃል
ዛሬም ፡ እረኛህ ፡ ፈልጐሃል
ሰምተሃል ፡ ድምጹን ፡ ወንድሜ ፡ ሆይ?
ልብህን ፡ ከፈትህ ፡ ወይ?
ምን ፡ ይሆናል ፡ ለሰማይ ፡ መናኝ
ድኖ ፡ ከአምላክ ፡ ጋራ ፡ ሲገናኝ
ምን ፡ ያህል ፡ ደስታ ፡ አለ ፡ በላይ
በቤቱ ፡ በሰማይ

ሳታመነታ ፡ ለርሱ ፡ ክፈት
ዛሬም ፡ ተቀበል ፡ ከእርሱ ፡ ሥርየት
ዛሬ ፡ ሲሰጥህ ፡ የአምላክ ፡ ፀጋ
ልብህን ፡ አትዝጋ
ምን ፡ ይሆናል ፡ ለሰማይ ፡ መናኝ
ድኖ ፡ ከአምላክ ፡ ጋራ ፡ ሲገናኝ
ምን ፡ ያህል ፡ ደስታ ፡ አለ ፡ በላይ
በቤቱ ፡ በሰማይ