ኢየሱስ ፡ መድኃኒትህ ፡ ልቡን ፡ ከፍቶልህ (Eyesus Medhanitih Libun Keftolih)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ኢየሱስ ፡ መድኃኒትህ ፡ ልቡን ፡ ከፍቶልህ
በዕቅፉ ፡ ሊቀበልህ ፡ ምኞቴ ፡ ነው
ምሉዕ ፡ ደኅንነትም ፡ ከተገኘልህ
ስለምን ፡ ጭንቁን ፡ የምትመርጠው
ታላቅ ፡ መሓሪው ፡ አንተን ፡ ይጠራል
ልብህን ፡ ስጠኝ ፣ በፍቅሩ ፡ ይላል
ስለምን ፡ ፀጋው ፡ በከንቱ ፡ ይቀራል?
ነፍሱንም ፡ ለአንተ ፡ ሲል ፡ ለውጧል

ጸድቋል ፡ ዓለም ፡ በጌታ ፡ በኢየሱስ
የኃጢአት ፡ መሥዋዕት ፡ ቀርቧል
ቅዱሱ ፡ ረከሰ ፡ እኛን ፡ ሊቀድስ
ሙቶም ፡ ሁላችንን ፡ አድኖናል
ደሙ ፡ ሲፈስስ ፡ ተደመሰሰ ፡ ዕዳው
ኃጢአታችንም ፡ ጠፍቶልናል
ስለ ፡ እሥረኞች ፡ ፈራጁ ፡ ተቀጣ
ታረቀ ፡ አምላክ ፡ ይበቃንማል

አሁን ፡ ለኅጥአን ፡ ብፅዕና ፡ ተሰጠ
የበደላችን ፡ ዕጥፍ ፡ ሆኗል
አዳም ፡ ሁላችንን ፡ እንዳበላሸ
ክርስቶስ ፡ ሁላችንን ፡ አበጅቷል
ምሉዕ ፡ ዓርነት ፡ ያገኙቱ ፡ ባሮች
ወደው ፡ ሊገዙ ፡ ይገባ ፡ ይሆን?
እኛስ ፡ ይልቅ ፡ ደስ ፡ ብሎን ፡ እንደ ፡ ልጆች
ቸር ፡ አባታችንን ፡ እናመስግን

ፈቃር ፡ መድኃኒቴ ፡ ሆይ! ትሩፋትህ
ለእኔ ፡ ተሰጠና ፡ የእኔ ፡ ይሁን
ስሜ ፡ ተጽፏል ፡ በመጽሐፍህ
ከልቤም ፡ አንሥተሃል ፡ ሸክሙን
አባትህን ፡ ሳትክድ ፡ ራስህንም
ስሜን ፡ ከቁስልህ ፡ አትፍቅም
ፍቅርህን ፡ ላከብረው ፡ እንዲህ ፡ ልበልም
ወጽመዱን ፡ በጠስህ ፡ አወጣኸኝም