ኢየሱስ ፡ መድሃኒቴ (Eyesus Medhanitie)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፦ ኢየሱስ ፡ መድሃኒቴ ፡ ጌታዬ
በአንተ ፡ ነው ፡ የጣፈጠው ፡ ኑሮዬ
ስለሆንክ ፡ ባለ ፡ ውለታዬ
አያቋርጥም ፡ ምሥጋናዬ

የእኔ ፡ ኢየሱስ ፡ ለእኔ ፡ ልዩ ፡ ነው
ፍቅሩ ፡ እንደማለዳ ፡ ጠል ፡ ነው
ሥጋና ፡ ደምን ፡ አልፎ ፡ ጅማትን
ጠልቆ ፡ ይገባል ፡ ያረካልል ፡ ውስጥን
የማያቋርጥ ፡ ደስታን ፡ የሚሰጥ
መራራ ፡ ኑሮን ፡ የሚያጣፍጥ
ከኢየሱስ ፡ ልብ ፡ የሚመነጨው
የፍቅር ፡ ዘይት ፡ ልቤን ፡ አራሰው

አዝ፦ ኢየሱስ ፡ መድሃኒቴ ፡ ጌታዬ
በአንተ ፡ ነው ፡ የጣፈጠው ፡ ኑሮዬ
ስለሆንክ ፡ ባለ ፡ ውለታዬ
አያቋርጥም ፡ ምሥጋናዬ

ምንም ፡ እንኳን ፡ ባልሄድ ፡ በመንገዱ
ባልከተልም ፡ ፍፁም ፡ ፈቃዱን
በእኔ ፡ በልጁ ፡ ሆዱ ፡ አይጨክንም
ገፍቶ ፡ ከቤቱ ፡ አያስወጣኝም
ቢቀጣኝም ፡ እንኳን ፡ በኃጢአቴ
ሆዱ ፡ ይራራልኛል ፡ አባቴ
ልጄ ፡ እያለ ፡ ያባብለኝል
ወደ ፡ እቅፉ ፡ ይመልሰኛል

አዝ፦ ኢየሱስ ፡ መድሃኒቴ ፡ ጌታዬ
በአንተ ፡ ነው ፡ የጣፈጠው ፡ ኑሮዬ
ስለሆንክ ፡ ባለ ፡ ውለታዬ
አያቋርጥም ፡ ምሥጋናዬ

ወረት ፡ የሌለበት ፡ ንጹህ ፡ ፍቅር
ትልቅ ፡ ትንሹን ፡ የሚያፈቅር
የሰው ፡ ማንነት ፡ ከቶ ፡ ያማይገደው
ቸሩ ፡ ኢየሱስ ፡ ሰፊ ፡ ሆድ ፡ አለው
ትልቁን ፡ እንደ ፡ ትልቅነቱ
ትንሹን ፡ እንደ ፡ ትንሽነቱ
ሁሉንም ፡ ያቅፋል ፡ ከነኮተቱ
አይገመትም ፡ ጥልቀት ፡ ስፋቱ

አዝ፦ ኢየሱስ ፡ መድሃኒቴ ፡ ጌታዬ
በአንተ ፡ ነው ፡ የጣፈጠው ፡ ኑሮዬ
ስለሆንክ ፡ ባለ ፡ ውለታዬ
አያቋርጥም ፡ ምሥጋናዬ

የልቤን ፡ ትርታ ፡ የሚያዳምጥ
ልጄ ፡ እያለ ፡ የሚያቆላምጥ
ትከሸው ሰፊ አባት ነው ያለኝ
እስከ ፡ እርጅና ፡ የሚሸከመኝ
በአባቴ ፡ ላይ ፡ ሃሳቤን ፡ ጥዬ
እኖራለሁኝ ፡ ተቀማጥዬ
በምንም ፡ ነገር ፡ አልጨነቅም
ስለነገውም ፡ ምንም ፡ አልውቅም

አዝ፦ ኢየሱስ ፡ መድሃኒቴ ፡ ጌታዬ
በአንተ ፡ ነው ፡ የጣፈጠው ፡ ኑሮዬ
ስለሆንክ ፡ ባለ ፡ ውለታዬ
አያቋርጥም ፡ ምሥጋናዬ