ኢየሱስ ፡ ልቤን ፡ ውሰድልኝ (Eyesus Lebien Wusedelegne)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ኢየሱስ ፡ ልቤን ፡ ውሰድልኝ
አንተ ፡ ተንከባከበኝ
ጉድለት ፡ ሁሉ ፡ ቢኖርብኝ
ለዘለዓለም ፡ የአንተ ፡ ነኝ
ሕይወትና ፡ ኃይል ፡ አጣለሁ
እወድቃለሁ ፡ ሁሉ ፡ ቀን
በአንተ ፡ ብቻ ፡ ተጥያለሁ
ከእናቴ ፡ ማኅጸን

እኔ ፡ አንድ ፡ ምስኪን ፡ ድሃ ፡ ነኝ
አንተ ፡ ሃብታም ፡ ጌታ ፡ ነህ
አንተም ፡ ከመሞት ፡ አዳንኸኝ
መቅሠፍቴን ፡ ተሸክመህ
ኃጢአቴም ፡ ቢያስፈራኝ
ዓይኔን ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ ሳብ
አንተ ፡ ከእርሱ ፡ ልታጠራኝ
አፍስሰሃል ፡ የደም ፡ ላብ

ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ የሠራህልኝ
ለዘለዓለም ፡ በቂ ፡ ነው
ሕግህም ፡ እንዳይፈርድብኝ
አንተ ፡ ራስህ ፡ ፈጸምኸው
አንተ ፡ ስትነግረኝም
አምኜ ፡ ልቀበለው
ሌላ ፡ አያስፈልገኝም
ፀጋህን ፡ ላመስግነው