ኢየሱስ ፡ ለዓለም ፡ ሲል ፡ ሙቷል (Eyesus LeAlem Sil Motoal)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ኢየሱስ ፡ ለዓለም ፡ ሲል ፡ ሙቷል
አምላክ ፡ ስጠኝ ፡ ቅዱስ ፡ ማስተዋል
እንድድንበት ፡ ከኩነኔ
እርሱ ፡ በመስቀል ፡ ሞተ ፡ ለእኔ

እንዴት ፡ ይገርማል ፡ ታላቅ ፡ ፍቅሩ
ማንም ፡ አይወደኝ ፡ እንደ ፡ እርሱ
እርሱ ፡ ካዳነኝ ፡ በመሞቱ
ሕይወቴን ፡ ልስጠው ፡ ለክብረቱ

አምላኬ ፡ ሆይ! ልጅህ ፡ አድርገኝ
ከሰይጣን ፡ ወጥመድ ፡ ሁሉ ፡ ፍታኝ
አንተን ፡ ልከተል ፡ አስተምረኝ
ለአንተም ፡ ልሆን ፡ በፍቅርህ ፡ እርዳኝ