ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ ወንድም ፡ ከሆነልኝ (Eyesus Kristos Wondem Kehonelegn)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ ወንድም ፡ ከሆነልኝ
ከእርሱም ፡ ጋራ ፡ የምወርስ ፡ ብሆን
ሐዘን ፡ ሁሉ ፡ ከእኔ ፡ ይራቅልኝ
የምጨነቅስ ፡ በምን ፡ ይሆን?
አምላካችን ፡ ወንድሜ ፡ ሆነልኝ
ነገሩ ፡ እንዴት ፡ ይገርመኛል?
ለአዕምሮዬም ፡ ባይታይልኝ
ቃሉ ፡ ፈጽሞ ፡ ያስረዳኛል

እርሱ ፡ አምላኬና ፡ አምላካችሁ
አባቴም ፡ የናንተ ፡ አባት ፡ ነው
የእኔ ፡ ወንድሞች ፡ እናንተ ፡ ናችሁ
ሲል ፡ ተስፋችን ፡ በእርሱ ፡ ምሉ ፡ ነው
እንደ ፡ ምኞቴ ፡ እንኳ ፡ ባይሰማኝ
ከቶ ፡ የእርሱ ፡ ቃል ፡ አይፋለስም
ነፍሴ ፡ ሆይ! ይህንን ፡ ቃል ፡ ስታገኚ
ምነው ፡ በእርሱ ፡ ደስ ፡ አላለሽም?

በሰው ፡ ሃሣብ ፡ ከቶ ፡ የማይመዘን
ግሩም ፡ የሆነ ፡ ወንድምነት ፡ ነው
ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ በሚወርሰው ፡ መጠን
ርስቴም ፡ ከእርሱ ፡ ጋራ ፡ እኩል ፡ ነው
በመሞቱ ፡ የተከፈተልኝ
መንግሥቱም ፡ ይቆየኛል ፡ በላይ
አምላኬ ፡ ሕዋሳቴን ፡ አብራልኝ
ርስቴንም ፡ ለዕምነቴ ፡ አሳይ