ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ ራሱ ፡ ሆነ (Eyesus Kristos Rasu Hone)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ ራሱ ፡ ሆነ
የእኔ ፡ ወዳጅ ።
ነፍሴንም ፡ ከሞት ፡ አዳነ
ያ ፡ ቸር ፡ ወዳጅ ።
ልቡናው ፡ በፍቅር ፡ ጋለ
እኛን ፡ ወንድሞቼ ፡ አለ
ለእኛም ፡ ሲል ፡ ሕይወቱን ፡ ጣለ
ያ ፡ ቸር ፡ ወዳጅ ።

ሳልገናኝህ ፡ ወደኸኛል
ኦ! ቸር ፡ ወዳጅ ።
በምሕረት ፡ ተዛምደኸኛል
እንደ ፡ ወዳጅ ።
ከጥፋቴ ፡ ስበኸኛል
ከመሞት ፡ አድነኸኛል
ለልጅነት ፡ መርጠኸኛል
ኦ! ቸር ፡ ወዳጅ ።

ሁልጊዜ ፡ ረድዔት ፡ እሻለሁ
ከዚህ ፡ ወዳጅ ።
ሁሉንም ፡ እነግራለሁ
ለዚህ ፡ ወዳጅ ።
አንዳች ፡ ነገር ፡ ቢሆንብኝ
ልመናዬን ፡ ሲሰማልኝ
ገርሞኛል ፡ ሲያስብልኝ
ይህ ፡ ግሩም ፡ ወዳጅ ።

ይህ ፡ ወዳጅ ፡ በሃዘን ፡ ሁሉ
ያ ጸ ና ኛ ል ።
እርሱም ፡ ኃጢአቴን ፡ ሁሉ
ይ ሠ ር ያ ል ።
እኔም ፡ ሁልጊዜ ፡ ስበድል
መከራዬን ፡ ሲያስተውል
በስሕተቴ ፡ ሳይበቀል
ይ ም ረ ኛ ል ።

እንዳይታየኝም ፡ ብደበቅ
አ ይ ተ ወ ኝ ም ።
እኔን ፡ ራሴን ፡ ለመጠበቅ
አ ይ ለ ቀ ኝ ም ።
መንገዱ ፡ ባይታወቀኝም
ሊረዳኝ ፡ ሊያድነኝም
ነውና ፣ ቢፈትነኝም
አ ላ ዝ ን ም ።

ሃሣብ ፡ ሁሉ ፡ እጥላለሁ
በዚህ ፡ ወዳጅ ።
ሁሉን ፡ እጠባበቃለሁ
ከዚህ ፡ ወዳጅ ።
አሮጌ ፡ ሥጋዬን ፡ መግደል
ነፍሴን ፡ ከጥፋት ፡ ማስጠለል
መከራዬንም ፡ ለማቅለል
ይ ቻ ለ ዋ ል ።

አምላክ ፡ የተዛመዳቸው
እንደ ፡ ወዳጅ ።
ለዘለዓለም ፡ ብሩካን ፡ ናቸው
ኦ! ግሩም ፡ ወዳጅ ።
ሌላ ፡ ዘመድ ፡ ሲተዋቸው
ሌላ ፡ ሃብት ፡ ሲጠፋባቸው
የዘለዓለም ፡ ሃብት ፡ አላቸው
በዚህ ፡ ወዳጅ ።