ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ የእኔ ፡ ወዳጅ (Eyesus Kerestos Yenie Wedaj)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ የእኔ ፡ ወዳጅ
እንደ ፡ እርሱ ፡ የለኝም
ሌሎችም ፡ እንኳ ፡ ቢተውኝ
እርሱስ ፡ አያደርገውም
ማን ፡ ነው ፡ አሁን ፡ የሚለየኝ?
ጌታዬ ፡ ከወደደኝ
አንድነት ፡ ከእርሱ ፡ አለኝ
ማንም ፡ የማይወስድብኝ

እርሱ ፡ ሞተ ፡ ስለ ፡ እኔ
ማነው ፡ የሚፈርድብኝ?
ከአባቱ ፡ ለመነልኝ
ለዘለዓለም ፡ ጠቀመኝ
ማነው ፡ አሁን ፡ የሚከሰኝ?
እርሱ ፡ ራሱ ፡ መረጠኝ
ማነው ፡ ከእርሱ ፡ የሚነጥቀኝ?
ጌታዬ ፡ ሲጠብቀኝ

ፍፁም ፡ ተስፋ ፡ አሁን ፡ አለኝ
ሞትም ፡ ሆነ ፡ ሕይወትም
ከጌታዬ ፡ አይለየኝም
ራብም ፡ ሆነ ፡ ጭንቀትም
ዝቅታም ፡ ከፍታም ፡ ሃዘን ፡ ችግር
አላፊ ፡ መጭም ፡ ቢሆን
ከዚህ ፡ ፍቅር ፡ አይለየኝም
በኢየሱስ ፡ ካገኘሁት