ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ የልቤ ፡ ተስፋ (Eyesus Hoy Yelebie Tesfa)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ የልቤ ፡ ተስፋ
ነፍሴን ፡ ደስ ፡ የምታሰኝ
በረከትን ፡ ለእኔ ፡ አስፋ
ከቃልህ ፡ ብርሃን ፡ ስጠኝ
ና ፡ ወደኔ ፡ ኢየሱስ ፡ ሆይ
ከእኔ ፡ ዘንድ ፡ ዘወትር ፡ ቆይ

በቅዱስ ፡ ስምህ ፡ ልጀምር
ዕለት ፡ ዕለት ፡ ሥራዬን
ምረቃን ፡ በላዩ ፡ ጨምር
እስክፈጽም ፡ ዕድሜዬን
ና ፡ ወደኔ ፡ ኢየሱስ ፡ ሆይ
ከእኔ ፡ ዘንድ ፡ ዘወትር ፡ ቆይ

የአፌን ፡ ቃል ፣ የልቤን ፡ ሃሣብ
በምሕረትህ ፡ እይልኝ
የማይጠፋ ፡ ሃብት ፡ ልሰብስብ
ለመማር ፡ ሠርክ ፡ ቀስቅሰኝ
ና ፣ ወደኔ ፡ ኢየሱስ ፡ ሆይ
ከእኔ ፡ ዘንድ ፡ ዘወትር ፡ ቆይ

ለመተኛት ፡ ሲመሽብኝ
ጠብቀኝ ፡ ቸሩ ፡ ጌታ
አትራቅ ፡ ቀን ፡ ሲነጋልኝ
ኢየሱስ ፡ ሁን ፣ ከእኔ ፡ ጋራ
ና ፣ ወደኔ ፡ ኢየሱስ ፡ ሆይ
ከእኔ ፡ ዘንድ ፡ ዘወትር ፡ ቆይ