ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ የአንተ ፡ ሕማማት (Eyesus Hoy Yante Himamat)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ኢየሱስ ፡ ሆይ! የአንተ ፡ ሕማማት
የአንተ ፡ ቁስልና ፡ ሞት
ይሰጠኛል ፡ መጸናናት
በሚደርስብኝ ፡ ጭንቀት
ሥጋዬ ፡ ቢፈትነኝ
ሕማምህን ፡ አሳስበኝ
ጉዳት ፡ እንዳይወርድብኝ
ሥጋዊ ፡ ምኞትን ፡ አጥቃልኝ

ክፉ ፡ ሥጋ ፡ ወደ ፡ ፍትወት
ቢያስመኘኝ ፡ ለውድቀት
ቁስልህን ፡ ግን ፡ ስመለከት
ሊሆነኝ ፡ አዲስ ፡ ድፍረት
ሰይጣንም ፡ ቢፈትነኝ
የፀጋህን ፡ ኃይል ፡ ሳገኝ
በቶሎ ፡ እስኪሸሽልኝ
ለማሸነፍ ፡ ልታበቃኝ

ኢየሱስ ፡ ሆይ! የልቤ ፡ጌታ
በውስጤ ፡ ከኖርህልኝ
ጭንቅ ፡ ምንም ፡ እንኳ ፡ ቢበዛ
ከሰላምህ ፡ አይለየኝ
ዋጀኸኝ ፡ ለአንተ ፡ ነኝ
ምን ፡ አለ ፡ የጐደለኝ?
ሁሉ ፡ ከአንተ ፡ ጋራ ፡ ሳለኝ
ብጽዕናን ፡ አታስቀርብኝ