ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ ጤና ፡ ሰላምም ፡ ልትሰጠኝ (Eyesus Hoy Tena Selamem Litsetegn)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ኢየሱስ ፡ ሆይ!
ጤና ፡ ሰላምም ፡ ልትሰጠኝ ፡ ሞተሃል
በማይነገረው ፡ ሕማምም
ነፍሴን ፡ ከሞት ፡ ገዝተሃል
ከጥፋት ፡ አሁን ፡ ድኛለሁ
ሕይወትንም ፡ እወርሳለሁ
ይሁንልህ ፡ ውዳሴ
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ አምላኬ!

ስለ ፡ መረረ ፡ ሕማምህ
ልቤ ፡ ያመሰግናል
በሥቃይህ ፡ በድካምህ
ሕይወት ፡ ተገኝቶልኛል
ልትሠርይ ፡ የእኔን ፡ በደል
ሞትን ፡ ቀምሰሃል ፡ በመስቀል
ይሁንልህ ፡ ውዳሴ
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ አምላኬ!