From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
|
ሌሎች ፡ የድሮ ፡ መዝሙሮች (Other Classic Mezmur Lyrics)
|
|
አዝ ፣
::ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ በል ፡ ልበልህ
ጌታ ፡ ሆይ ፡ ክበር ፡ ተመስገን ፡ ልበልህ
ወደር ፡ የማይገኝልህ
ከሞት ፡ ያድናል ፡ ስምህ ፪X
ስምህ ፡ እንደሚፈስ ፡ ዘይት ፡ ነው
ጠልቆ ፡ ወደ ፡ ውስጥ ፡ ይገባል
የደረቀውን ፡ አጥንት ፡ አረስርሶ
ስብራትን ፡ ይጠግናል
ሽባውን ፡ አዘልለህ
የዛለውን ፡ ጉልበት ፡ ታጸናለህ
ልብን ፡ ኩላሊትን ፡ መርምረህ
ለደካማ ፡ ኃይልን ፡ ትሰጣለህ ።
አዝ ፣
::ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ በል ፡ ልበልህ
ጌታ ፡ ሆይ ፡ ክበር ፡ ተመስገን ፡ ልበልህ
ወደር ፡ የማይገኝልህ
ከሞት ፡ ያድናል ፡ ስምህ ፪X
በነፍስ ፡ በሥጋ ፡ ሥልጣን ፡ አለህ
የበሽታን ፡ ሥር ፡ ነቅለህ ፡ ትጥላለህ
የታወረውን ፡ ዓይን ፡ አብርተህ
የጐበጠውን ፡ ታቃናለህ
ፍፁም ፡ ድንቅ ፡ ነው ፡ ስምህ ፡ ያድናል
የተጨነቁትን ፡ በሕመም
ከድቅድቅ ፡ ጨለማ ፡ ያወጣል
ወደሚደነቅ ፡ ብርሃን ።
አዝ ፣
::ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ በል ፡ ልበልህ
ጌታ ፡ ሆይ ፡ ክበር ፡ ተመስገን ፡ ልበልህ
ወደር ፡ የማይገኝልህ
ከሞት ፡ ያድናል ፡ ስምህ ፪X
ጌታዬ! ስምህ ፡ ኃይል ፡ አለው
አጋንንትን ፡ ይቀጠቅጣል
ለስሜትም ፡ ከመገዛት
ከማይረባም ፡ ልማድ ፡ ያላቅቃል
ጥላቻንም ፡ አስወግዶ
ሁሉን ፡ አንድ ፡ ያደርጋል ፡ በፍቅር
መራራን ፡ ሕይወት ፡ ለውጦ
ያጣፍጠዋል ፡ እንደማር
አዝ ፣
::ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ በል ፡ ልበልህ
ጌታ ፡ ሆይ ፡ ክበር ፡ ተመስገን ፡ ልበልህ
ወደር ፡ የማይገኝልህ
ከሞት ፡ ያድናል ፡ ስምህ ፪X
በዕምነት ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ የቀረበ
በሕያው ፡ ስምህ ፡ ይድናል
ከሞት ፡ ባሻገር ፡ ያለውን
የዘላለምን ፡ ሕይወት ፡ ይወርሳል
ቸሩ ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ
በዕውነት ፡ አንተ ፡ ፍቅር ፡ ነህ
ልዑል ፡ እግዚአብሔር ፡ ሆይ!
ከፍ ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ በል ፡ ልበልህ ።
አዝ ፣
::ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ በል ፡ ልበልህ
ጌታ ፡ ሆይ ፡ ክበር ፡ ተመስገን ፡ ልበልህ
ወደር ፡ የማይገኝልህ
ከሞት ፡ ያድናል ፡ ስምህ ፪X
|