ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ ሕጻናትን ፡ በዕቅፍህ ፡ ውስጥ (Eyesus Hoy Hitsanatin Beiqifih Wustt)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ ሕጻናትን
በዕቅፍህ ፡ ውስጥ ፡ ተቀበልሃቸው
እኛም ፡ ቅዱስ ፡ ተስፋህን
አምነን ፡ ስናቀርባቸው
በአንተም ፡ ሥም ፡ ስናጠምቃቸው
ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ ተቀበላቸው

ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ የአንተ ፡ ደም
በዓብ ፡ ፊት ፡ ይቀድሳቸው
መንፈስህ ፡ በዕምነትም
ከአንተ ፡ ጋር ፡ ያሳብራቸው
ምሉዕ ፡ ፅድቅህን ፡ ይልበሱ
መንግሥትህንም ፡ ይውረሱ

ታናሾቹ ፡ በጐችህ
በእረኛቸው ፡ እጅ ፡ ይሁኑ
ሠርክ ፡ በጠባብ ፡ መንገድህ
ሂደው ፡ ከዓለም ፡ ሸር ፡ ይዳኑ
ርስትህ ፡ እንዳይጠፋባቸው
ኢየሱስ ፡ ሆይ! ና ፣ ጠብቃቸው