ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ በዚህ ፡ በምድር (Eyesus Hoy Bezih Bemeder)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ በዚህ ፡ በምድር
የማርፍበት ፡ የት ፡ ላግኝ?
ወደ ፡ ሰማያዊ ፡ አገር
አምጥተህ ፡ አሳርፈኝ
እመኛለሁ ፡ እመኛለሁ
ከአንተ ፡ ጋራ ፡ ልገናኝ

የምራመድበት ፡ መንገድ
እጅግ ፡ ቀጭን ፡ ሆኗል
ሰይጣንም ፡ በብዙ ፡ ወጽመድ
ሊያጸምደኝ ፡ ይጥራል
ጐዳናዬም ፡ ጐዳናዬም
በሞት ፡ ወንዝ ፡ ይወስደኛል

በዚህ ፡ በምፈራው ፡ ሁሉ
አንተ ፡ አደፋፍረኝ
የተሰጠውን ፡ ለዓለም ፡ ሁሉ
ደምህን ፡ አሳስበኝ
የአንተ ፡ መስቀል ፡ የአንተ ፡ መስቀል
ለእኔ ፡ ሕይወትን ፡ ይስጠኝ

አንዲት ፡ ቀን ፡ ስንኳ ፡ ሥጋዬን
ድል ፡ ለመንሣት ፡ አቃተኝ
ቅዱስ ፡ መንፈስህ ፡ ሥራዬን
መርቶ ፡ ምክሩን ፡ ይስጠኝ
ና ፡ ኦ ፡ ኢየሱስ ፤ ና ፡ ኦ ፡ ኢየሱስ
በድካሜ ፡ ኃይል ፡ ሁነኝ

ያለም ፡ ፍቅር ፡ ያለም ፡ ጥልም
ከቶ ፡ እንዳይደልለኝ
ቢገዛልኝ ፡ ምሉ ፡ ዓለም
ያለ ፡ አንተ ፡ ግን ፡ አይብቃኝ
አንተ ፡ ብቻ ፣ አንተ ፡ ብቻ
በእውነት ፡ መንገድህ ፡ ምራኝ

ወደ ፡ ርኅሩኅ ፡ ልብህ ፡ ሳበኝ
በእርሱ ፡ ውስጥም ፡ ሠውረኝ
ሌላም ፡ ሁሉ ፡ ቢጠፋብኝ
ከአንተ ፡ ጋራ ፣ ብፁዕ ፡ ነኝ
ከአንተር ፡ ጋራ ፣ ከአንተ ፡ ጋራ
የሰማይ ፡ ሰላም ፡ አለኝ