ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ አትለፍብኝ (Eyesus Hoy Atelefebegn)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ አትለፍብኝ
ፀሎቴን ፡ ስማኝ
ሌሎች ፡ ፀጋህን ፡ ሲያገኙ
አትለፍብኝ

አዝ፦ ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ ፀሎቴን ፡ ስማኝ
ሌሎች ፡ ፀጋህን ፡ ሲያገኙ
አ ት ለ ፍ ብ ኝ

ወደ ፡ ዘለዓለም ፡ ዙፋንህ
እመጣለሁኝ
ይቅርታህን ፡ ለመቀበል
እርዳኝ ፡ አቤቱ

አዝ፦ ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ ፀሎቴን ፡ ስማኝ
ሌሎች ፡ ፀጋህን ፡ ሲያገኙ
አ ት ለ ፍ ብ ኝ

ስለ ፡ ደግነትህ ፡ ብቻ
ጸጋህን ፡ ስጠኝ
የቆሰለ ፡ ልቤን ፡ ፈውስ
በፀጋህ ፡ ልዳን

አዝ፦ ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ ፀሎቴን ፡ ስማኝ
ሌሎች ፡ ፀጋህን ፡ ሲያገኙ
አ ት ለ ፍ ብ ኝ

አንተ ፡ ነህ ፡ የደስታ ፡ ምንጭም
ሕይወት ፡ አንተ ፡ ነህ
በሰማይና ፡ በምድር
ሌላ ፡ የለኝም

አዝ፦ ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ ፀሎቴን ፡ ስማኝ
ሌሎች ፡ ፀጋህን ፡ ሲያገኙ
አ ት ለ ፍ ብ ኝ