ኢየሱስ ፡ ሆነ ፡ ተስፋዬ (Eyesus Hone Tesfaye)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ኢየሱስ ፡ ሆነ ፡ ተስፋዬ
ሞትን ፡ ሽሮ ፡ ተነሣልኝ
ዕውነቱን ፡ ተረድቼ
ሃዘን ፡ እንዴት ፡ ሊመርብኝ
የሞት ፡ ሌሊት ፡ ያልፋል
ጨለማው ፡ ይሻራል

ሕያው ፡ ነው ፡ መድኃኒቴ
እኔም ፡ ሕይወትን ፡ ልወርስ
ይተባበራል ፡ ከእኔ
ምን ፡ ሰበብ ፡ አለኝ ፡ ለማልቀስ?
ቸር ፡ አባት ፡ ከፍቶ ፡ ቤቱን
ያከማቻል ፡ ልጆቹን

ከእርሱ ፡ ዘንድ ፡ ተባብሬ
ከእኔ ፡ ጋር ፡ ኪዳን ፡ ተጋባ
በዕምነት ፡ እስከ ፡ ሞቴ
አለኝ ፡ ፅኑ ፡ ብፁዕ ፡ ተስፋ
ከጌታ ፡ የሚለየኝ
አንድ ፡ እንኳ ፡ በዓለም ፡ አይገኝ

ከንቱ ፡ ሥጋ ፡ ነኛ
እኔ ፡ ለመሬት ፡ ልመለስ
ያስነሣኛል ፡ ግን ፡ ጌታ
ክቡር ፡ መንግሥቱን ፡ ልወርስ
ከመድኃኒቴ ፡ ጋራ
ልነግሥ ፡ ነኝ ፡ በብፅዕና

በሽታ ፡ ሥቃይ ፡ ያማቀቀው
ወዲያ ፡ ድኖ ፡ ይለማል
በውርደት ፡ የሚዘራው
ቆይቶ ፡ በክብረት ፡ ይነሣል
የአሁኑ ፡ ሃምህምታ
ሊለወጥ ፡ ለዕልልታ

ደስ ፡ ብሏችሁ ፡ ዘምሩ
ኢየሱስ ፡ ልጆቹን ፡ ይጦራል
ስለ ፡ ሞት ፡ አትዘኑ
ብንሞት ፡ ግን ፡ ያስነሣናል
ሙታን ፡ ደምፁን ፡ ሲሰሙ
ከመቃብር ፡ ሊወጡ

ራቁ ፡ ከከንቱነቷ
በኅዚህ ፡ ዓለም ፡ አትዛቡ
ልትሞቱ ፡ በተስፋ
በሰማይ ፡ ያለውን ፡ እሹ
ብትመኙ ፡ ብፅዕናን
አሁን ፡ ሁኑ ፡ ቅዱሣን