ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ ጌትነቱን (Eyesus Gieta New Gietenetun)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

በላይ ፡ በጸባዖት ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው
በታችም ፡ በምድር ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው
በከፍታ ፡ ስፍራ ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው
በዝቅታም ፡ ስፍራ ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው

አዝኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው (፪x)
ጌትነቱን ፡ የሚቃወም ፡ ማነው?
ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው

ከበሽታ ፡ ሁሉ ፡ ኢየሱስ ፡ ያድናል
የነፋስን ፡ ስብራት ፡ እርሱ ፡ ይፈወሳል
ከችግርም ፡ በላይ ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው
ምን ፡ አለ ፡ የሚሳነው ፡ ሁሉ ፡ በሁሉ ፡ ነው

አዝኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው (፪x)
ጌትነቱን ፡ የሚቃወም ፡ ማነው?
ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው

ሰላም ፡ በጠፋበት ፡ ኢየሱስ ፡ ሰላም ፡ ነው
እርካታንም ፡ ላጣ ፡ ኢየሱስ ፡ አርኪ ፡ ነው
ለጭንቀት ፡ መድሃኒት ፡ ኢየሱስ ፡ ፈውስ ፡ ነው
ፍቅሩ ፡ አይለወጥም ፡ ኢየሱስ ፡ ፍቅር ፡ ነው

አዝኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው (፪x)
ጌትነቱን ፡ የሚቃወም ፡ ማነው?
ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው

የኃይላት ፡ ሁሉ ፡ ኃይል ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው
ከአማልክት ፡ በላይ ፡ ኢየሱስ ፡ አምላክ ፡ ነው
በሰማይ ፡ በምድር ፡ ሙሉ ፡ ስልጣን ፡ አለው
ጌትነቱን ፡ ከቶ ፡ የሚቃወም ፡ ማነው?

አዝኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው (፪x)
ጌትነቱን ፡ የሚቃወም ፡ ማነው?
ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው

መልካም ፡ እረኛችን ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው
ልጆቹን ፡ በሰላም ፡ ሁሌ ፡ የሚጠብቅ ፡ ነው
ዘመን ፡ አይሽረውም ፡ ኢየሱስ ፡ ሕያው ፡ ነው
እንዲያው ፡ በደፈናው ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው

አዝኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው (፪x)
ጌትነቱን ፡ የሚቃወም ፡ ማነው?
ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው