ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው (Eyesus Gieta New)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ግርማውን ፡ አየን ፡ እኛን ፡ ሲመራን
ድል ፡ እየሰጠን ፡ ሲያለመልመን
ክንዱ ፡ ከቦናል ፡ ጥላው ፡ ጋርዶኛል
ውዱ ፡ ኢየሱስ ፡ ምሽግ ፡ ሆኖናል

አዝ፦ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው (፬x)

የአምላክ ፡ ጉልበቱ ፡ የማዳን ፡ ኃይሉ
እጅግ ፡ ደንቆናል ፡ ውለታው ፡ ሁሉ
ከአፈር ፡ አንስቶ ፡ እኛን ፡ ለወጠን
በመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ በእሳቱ ፡ ሞላን (፪x)

አዝ፦ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው (፬x)

ፍቅሩ ፡ በዛልን ፡ አረሰረሰን
ኢየሱስ ፡ ለእኛ ፡ ከዕንቁ ፡ በለጠ
በወንጌል ፡ እውነት ፡ ሁሉን ፡ አሸነፍን
በኢየሱስ ፡ ስም ፡ ድል ፡ በድል ፡ ሆንን (፪x)

አዝ፦ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው (፬x)