ኢየሱስ ፡ እንደወደደኝ (Eyesus Endewededegn)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ኢየሱስ ፡ እንደወደደኝ
ቅዱስ ፡ ወንጌል ፡ ነገረኝ
የእርሱ ፡ ናቸው ፡ ታናሾች
ኃይልም ፡ ነው ፡ ለደካሞች

አዝ፦ እኔን ፡ ይወዳል ፡ እኔን ፡ ይወዳል
እንደሚወደኝ ፡ ወንጌሉ ፡ ነገረኝ

ኢየሱስ ፡ ስለወደደኝ
በሰማይ ፡ ልግባ ፡ ነኝ
በደሌን ፡ ይቅር ፡ ይላል
ትንሽ ፡ ልጁን ፡ ያቅፋል

አዝ፦ እኔን ፡ ይወዳል ፡ እኔን ፡ ይወዳል
እንደሚወደኝ ፡ ወንጌሉ ፡ ነገረኝ

ኢየሱስም ፡ አይተወኝም
ቤቱን ፡ አይዘጋብኝም
ሁልጊዜ ፡ ይረዳኛል
በእጁም ፡ ይመራኛል

አዝ፦ እኔን ፡ ይወዳል ፡ እኔን ፡ ይወዳል
እንደሚወደኝ ፡ ወንጌሉ ፡ ነገረኝ