ኢየሱስ ፡ በጣም ፡ ይወደኛል (Eyesus Betam Yewedegnal)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፦ ኢየሱሴ ፡ በጣም ፡ ይወደኛል
የእኔስ ፡ ነገር ፡ አይሆንለትም
የእኔንስ ፡ ጉዳይ ፡ አይሆንለትም
ኢየሱሴ ፡ በጣም ፡ ይወደኛል
ሳዝን ፡ እቅፍ ፡ አድርጐ ፡ ያጽናናኛል
አውሬም ፡ እንዳይበላኝ ፡ ይጠብቀኛል
እንደእርሱ ፡ ያለ ፡ የት ፡ ይገኛል

እርሱ ፡ ነው ፡ በፍቅሩ ፡ ወደእራሱ ፡ የሳበኝ
የያዕቆብ ፡ አምላክ ፡ ለእኔም ፡ አምላኬ ፡ ነው
ዛሬም ፡ አልተወኝም ፡ ይመስገን ፡ ነው
የያዕቆብ ፡ አልጣለኝም ፡ ይመስገን ፡ ነው

አዝ፦ ኢየሱሴ ፡ በጣም ፡ ይወደኛል
የእኔስ ፡ ነገር ፡ አይሆንለትም
የእኔንስ ፡ ጉዳይ ፡ አይሆንለትም
ኢየሱሴ ፡ በጣም ፡ ይወደኛል
ሳዝን ፡ እቅፍ ፡ አድርጐ ፡ ያጽናናኛል
አውሬም ፡ እንዳይበላኝ ፡ ይጠብቀኛል
እንደእርሱ ፡ ያለ ፡ የት ፡ ይገኛል

ፍልስጤም ፡ በበቀል ፡ ሊያርደኝ ፡ ሲያሳድደኝ
ለካስ ፡ አልተወኝም ፡ ያኔ ፡ የወደደኝ
ያ ፡ ኃይለኛ ፡ አምላክ ፡ አበረታኝና
ጠላቴን ፡ እረገጥኩ ፡ እንደገና
ያ ፡ ጉልበታም ፡ አምላክ ፡ ጉልበት ፡ ሆነኝና
ጠላቴን ፡ ድል ፡ አደረግሁ ፡ እንደገና

አዝ፦ ኢየሱሴ ፡ በጣም ፡ ይወደኛል
የእኔስ ፡ ነገር ፡ አይሆንለትም
የእኔንስ ፡ ጉዳይ ፡ አይሆንለትም
ኢየሱሴ ፡ በጣም ፡ ይወደኛል
ሳዝን ፡ እቅፍ ፡ አድርጐ ፡ ያጽናናኛል
አውሬም ፡ እንዳይበላኝ ፡ ይጠብቀኛል
እንደእርሱ ፡ ያለ ፡ የት ፡ ይገኛል

የጠላቴን ፡ ዛቻ ፡ ስሸሽ ፡ ፈርቼ
ከክትክታ ፡ በታች ፡ እንቅልፌን ፡ ተኝቼ
ቀሰቀሰኝና ፡ እንጐቻን ፡ አበላኝ
የዘለዓለም ፡ አምላክ ፡ አስተማረኝ
ቀሰቀሰኝና ፡ እንጐቻ ፡ አበላኝ
የናዝሬቱ ፡ ኢየሱስ ፡ አስተማረኝ

አዝ፦ ኢየሱሴ ፡ በጣም ፡ ይወደኛል
የእኔስ ፡ ነገር ፡ አይሆንለትም
የእኔንስ ፡ ጉዳይ ፡ አይሆንለትም
ኢየሱሴ ፡ በጣም ፡ ይወደኛል
ሳዝን ፡ እቅፍ ፡ አድርጐ ፡ ያጽናናኛል
አውሬም ፡ እንዳይበላኝ ፡ ይጠብቀኛል
እንደእርሱ ፡ ያለ ፡ የት ፡ ይገኛል

ዝርግፍ ፡ ጌጤ ፡ ኢየሱስ ፡ ውበት ፡ ሆኖልኛል
በሥጋና ፡ በነፍስ ፡ ሁሌ ፡ ይባርከኛል
ዘመድ ፡ አለነበረኝ ፡ እርሱ ፡ ሆነኝ ፡ ወገን
ስሙ ፡ ለዘለዓለም ፡ ይመስገን
ወገን ፡ አልነበረኝም ፡ እርሱ ፡ ሆነኝ ፡ ወገን
እግዚአብሔር ፡ አምላኬ ፡ ይመስገን

አዝ፦ ኢየሱሴ ፡ በጣም ፡ ይወደኛል
የእኔስ ፡ ነገር ፡ አይሆንለትም
የእኔንስ ፡ ጉዳይ ፡ አይሆንለትም
ኢየሱሴ ፡ በጣም ፡ ይወደኛል
ሳዝን ፡ እቅፍ ፡ አድርጐ ፡ ያጽናናኛል
አውሬም ፡ እንዳይበላኝ ፡ ይጠብቀኛል
እንደእርሱ ፡ ያለ ፡ የት ፡ ይገኛል

እንዲህ ፡ የወደደኝ ፡ ምን ፡ አድርጌለት ፡ ነው
ከገሃነመ ፡ እሳት ፡ ሕይወቴን ፡ ያዳነው
ሳላውቀው ፡ አወቀኝ ፡ ሳልመርጠው ፡ መረጠኝ (፪x)
የዘለዓለምን ፡ ሕይወት ፡ ሰጠኝ

አዝ፦ ኢየሱሴ ፡ በጣም ፡ ይወደኛል
የእኔስ ፡ ነገር ፡ አይሆንለትም
የእኔንስ ፡ ጉዳይ ፡ አይሆንለትም
ኢየሱሴ ፡ በጣም ፡ ይወደኛል
ሳዝን ፡ እቅፍ ፡ አድርጐ ፡ ያጽናናኛል
አውሬም ፡ እንዳይበላኝ ፡ ይጠብቀኛል
እንደእርሱ ፡ ያለ ፡ የት ፡ ይገኛል